፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ታህሳስ 25 2017| NBC ETHIOPIA- በደቡባዊ ካሊፎርኒያ ፉለርተን ከተማ አነስተኛ አውሮፕላን ተከስክሶ የሁለት ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰምቷል፡፡
አደጋውን ተከትሎ የፉለርተን ከተማ ፖሊስ በሰጠው ማብራሪያ ሕይወታቸው ካለፈው ሰዎች በተጨማሪ በ18 ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን አስታውቋል፡፡ የአደጋው መንስዔም እየተጣራ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ ዘገባው የሲ ኤን ኤን ነው፡፡












