፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ህዳር 06 2017| NBC ETHIOPIA-የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በሀገሪቱ ከሚገኙ 51 የመንግስት እና አምስት የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ማህበረሰብ ተወካዮች ጋር ውይይት በማካሄድ ላይ ይገኛል።
እስካሁን በዘጠኝ ክልሎች እና ሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች በተደረገው አጀንዳ የማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ ከ105 ሺህ በላይ ተወካዮች መሳተፋቸው በመድረኩ ተገልጿል።
ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በምክክሩ ያላቸውን ሚና ለማጎልበት ባለመው በዛሬው መድረክ 1200 የዩኒቨርሲቲዎች ከፍተኛ ሃላፊዎች ብሎም የተለያዩ ሃላፊዎች ተሳታፊ ሆነውበታል።


ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በእስካሁኑ ሂደት ጉልህ አስተዋፅኦ ሲያበረክቱ መቆየታቸውን የገለፁት ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን ዓርዓያ ምሁራን ለጋራ ችግር የጋራ መፍትሄ ይመጣ ዘነድ ሙያዊ ሃላፊነት አለባቸው ብለዋል።
መርሃ ግብሩ ኮሚሽኑ እስካሁን የሰራቸው ስራዎች፣ በእስካሁኑ ሂደት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የነበራቸው ሚና እንዲሁም በሂደቱ ያጋጠሙ ችግሮች እና ተግዳሮቶች የሚዳሰሱበት ይሆናል።


ኮሚሽኑ እና ተቋማቱ በቀጣይ በጋራ ሊሰሩ በሚችሉባቸው ሁኔታዎች ላይ የሚመክሩ ሲሆን ተሳታፊዎች ጥያቄ እና ሃሳቦቻቸውን አቅርበው ምላሽ የሚያገኙበት የውይይት መድረክም የመርሃ ግብሩ አካል ነው።
በ-መቅደስ ደምስ
📌YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
📌 TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
📌Facebook- https://web.facebook.com/ethiopiannbc/
📌Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
#NBCEthiopia
#ሆኖ_መገኘት












