ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ቀናት ደቡብ ኮሪያ የሰው አልባ የጦር አውሮፕላኖቿን ወደ ሰሜን ኮሪያ ድንበር መላኳ ሲገለጽ ሰሜን ኮሪያ በበኩሏየሁለቱን ሀገራት የጋራ መጠቀሚያ መንገድ ሰሜናዊ ክፍሉን ጨርሶ ለማውደም መዠጋጀቷን ነው ደቡብ ኮሪያ ያስታወቀችው፡፡

አሁን ሰሜን ኮሪያ ልታወድመው ተዘጋጅታለች የሚባልለት መንገድ ከዚህ በኋላ ምንም ጥቅም እንደማይሠጥ ነው የደቡብ ኮሪያ ባለስልጣናት የገለጹት።
ሰሜን ኮሪያ በበኩሏ ደቡብ ኮሪያ ባንድ ወር ጊዜ ውስጥ ብቻ ለሶስተኛ ጊዜ የሰው አልባ የጦር አውሮፕላኖቿን በድንበሬ አቅራቢያ አስጠግታለች ስትል ትከሳለች ዘገባው የቦርኔኦ ቡሌቲን ነው፡፡
በ-ትዕግስቱ በቀለ












