የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የምንገኝበት ወቅት እድልና ተወዳድሪ ተግዳሮት ያለበት ነው ያሉ ሲሆን ዛሬ እውቅና የተሰሰጣቸው ተማሪዎች ችግሮቹን ማለፍ የቻሉ ናቸው ብለዋል።
በተከታታይ ዓመታት በ12ኛ ክፍል ሀገር አቅፍ ፈተና ላይ የውጤት ማሽቆልቆል መታየቱ እንደሀገር ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሰራ አድርጓል።ዘንድሮ የተገኘው ውጤት መሻሻል የተየበት እንደሆነ ገልጸዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ሽልማቱ ከፍተኛ ውጤት ያመጡትን በማበረታት ችግር ፈቺ ስራ እንዲሰሩ የሚያደርግ ሲሆን ሌሎች ተማሪዎችን ደግሞ እንደሚችሉ ያሳየ ነው ብለዋል።
የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ኃላፉ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ በ2016 የትምህርት ዘመን የ12 ክፍል ተማሪዎች ውጤት ከአምናው የተሻለ መሆኑን ተናግረዋል።
በተለይ ሴቶች ተማሪዎች ይበልጥ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡበት ነበር ብለዋል።ዝቅተኛ ተማሪዎች ያሳለፉ የትምህርት ተቋማት ላይ እንዲሁም በሂሳብና በእንግሊዝኛ የትምህርት አይነቶች ላይ ጠንካራ ስራ እንደሚሰራ ተመላክቷል።
እንዲሁም ደረጃውን የጠበቀ የትምህርት ምህዳር ለመፍጠር ትምህርት ቤቶች ማሻሻል እና የትምህርት ስርዓቱን መገንባት ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ በመድረኩ ተመላክቷል።
በ-ሰላም ይልማ












