፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መስከረም 27 2017| NBC ETHIOPIA- የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሆነው በአብላጫ ድምጽ የተሾሙት አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ቃለ መሃላን ፈጽመዋል፡፡
የምትሻገር ሀገር በማይሻገር ሐሳብ እየተናጠች ቆይታለች ሲሉ በሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ- ሥርዓት የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል፡፡
ከጥቅምት 15 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ የመጀመሪያዋ ሴት ርዕሰ ብሔር ሆነው ሀገርን ሲያገለግሉ የቆዩት ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ለአዲሱ ፕሬዝዳንት ሥልጣኑን አስረክበዋል፡፡
በአሕጉር አፍሪካ ሴት ፕሬዝዳንት በመሆን በአሕጉሪቱ በልዩነት የሚጠቀሱት ሳሕለ ወርቅ ዘውዴ እና የታንዛንያ ፕሬዝዳንት Samia Suluhu Hassan መሆናቸውን የAfrica Faith and Justice Network መረጃ ያሳያል፡፡
ከሦስት አስርት ዓመታት በላይ በዓለም አቀፍ ግንኙነት እና በዲፕሎማቲክ መስክ አገራቸውን ያገለገሉት አምባሳደር ታዬ፣ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት፣ በተለያዩ አገራት እንዲሁም በመንግሥታቱ ድርጅት በሙያቸው ሀገርን ሲያገለግሉ የቆዩ ምንም እንኳን በተለያዩ ሥርዓተ መንግስታት ፕሬዝዳንቶች ቢኖሩም ለኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዌ ሪፐብሊክ ግን አምስተኛ ፕሬዝዳንት በመሆን የተመረጡ ናቸው፡፡
ፕሬዝዳንት ታዬ ከአንጋፋው ተቋም አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በፖለቲካል ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው ሲሆን፣ ከእንግሊዙ ላንካስተር ዩኒቨርስቲ ደግሞ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን በዓለም አቀፍ ግንኙነት እና በስትራቴጂክ ጥናቶች አግኝተዋል።
በ-ፍቅረሚካኤል ዘየደ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












