፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መስከረም 22 2017| NBC ETHIOPIA- በጅቡቲ የውሀ ጠረፍ ስትቀዝፍ የነበረች ጀልባ ባጋጣማት የመስመጥ አደጋ በርካታ ሰዎች መሞታቸው ተነግሯል፡፡
የመንግስታቱ ድርጅት የስደተኞች መረጃ ተቋም ባወጣው መግለጫው ከአፍሪካ ሀገራት ስደተኞችን የጫኑ ሁለት ጀልባዎች በጅቡቲ ጠረፍ መስመጣቸውን ተከትሎ በትንሹ 45 ሰዎች መሞታቸውን ሲገለጽ በደርዘን የሞቆጠሩ ሌሎች ደግሞ የደረሱበት መጥፋቱ ተነግሯል፡፡

የአለም አቀፍ የስደተኞች መረጃ ተቋም አይ ኦ ኤም በሰጠው ማብራሪያ ጀልባዎቹ በቀይ ባህር አልፈው ወደ የመን ለመድረስ ከ310 በላይ ስደተኞችን አሳፍረው እንደነበር አስታውቋል፡፡
በ-ትዕግስቱ በቀለ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












