፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መስከረም 20 2017| NBC ETHIOPIA- የደሴ ከተማ አስተዳደር በ2017 ዓ.ም ከሚያከናውናቸው የልማት ሥራዎች መካከል አንዱ የኾነውን የኮሪደር ልማት ለማስጀመር ውይይት እና የመስክ ምልከታ ተካሂዷል።
የደሴ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ሳሙኤል ሞላልኝ በ2017 ዓ.ም የኮሪደር ልማትን ተግባራዊ ለማድረግ ወደ ሥራ መገባቱን ጠቅሰው ለዚህም ለኮሪደር ልማቱ ቦታዎች መለየታቸውን እና በቀጣይ ወር ወደ ትግበራ እንደሚገባ ተናግረዋል።

አቶ ሳሙኤል ከዚህ ቀደም የተሠሩ ሥራዎች አሁን ለተጀመረው የኮሪደር ልማት ምቹ ሁኔታ መፍጠራቸውን ገልጸው አሁንም እንደ ቀድሞው ሕዝብን ታሳቢ ያደረገ ሥራ ይሠራል ብለዋል።
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለደሴ እና ሰመራ ከተማ የኮሪደር ልማት አስተባባሪ ሆነው የተመረጡት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር ዓባይ የደሴ መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ እና የምህንድስና ጥበብን ተጠቅሞ ምቹ የኮሪደር ልማት ለመሥራት መልካም አጋጣሚ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ከተሞች በመንግሥት ልፋት እና ጥረት ብቻ ሊለወጡ አይችሉም ያሉት አቶ ጃንጥራር ከአዲስ አበባ ልምድ በመቅሰም የግሉ ባለሃብትም የድርሻውን በማበርከት ተባባሪ መሆን ይገባዋል ብለዋል ዘገባ የአማራ ኮሙኒኬሽን ነው፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












