፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መስከረም 20 2017| NBC ETHIOPIA- በኔፓል በተከሰተው የጎርፍና የመሬት መንሸራተት አደጋ በርካታ ሰዎች ህይወታቸውን ማጣታቸውን ተገልጿል፡፡

በኔፓል ለሁለት ቀናት የጣለው ከባድ ዝናብና ያስከተለው ጎርፍ እንዲሁም ዝናቡንና ጎርፉን ተከትሎ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ደግሞ 170 ሰዎች መሞታቸውና በደርዘን የሚቆጠሩ ሌሎች ሰዎች መጥፋታቸው ነው የተሰማው፡፡ ኔፓል የገጠማት ከባድ የተፈጥሮ አደጋ አስመልክታም ለሶስት ቀና ትምህርት ቤቶቿን መዝጋቷ ነው የተገለፀው፡፡
ከዚያም ውጪ የየብስ ትራንስፖርት ዝግ ሆኖ መቆየቱ ሲነገር በረራዎች ከካታማንዱ መሰረዛቸውን የዳውን ዘገባ ያስረዳል፡፡
በ-ትዕግስቱ በቀለ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbcv
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












