፨ ፨ ፨ ፨ ፨
ኢትዮጵያ በቀጣይ ወራት ከፍተኛ ዝናብ ታስተናግዳለች ተባለ
፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 29 2016| NBC ETHIOPIA- የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ኢትዮጵያ በቀጣይ የነሀሴ እና መስከረም ወራት ከፍተኛ ዝናብ እንደምታስተናግድ አስታውቋል።
ሀገሪቷ በሁለቱ ወራት ከመደበኛ በላይ የዝናብ መጠን ልታስናግድ ትችላለች ብለዋል የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ፈጠነ ተሾመ።
የአየር ሁኔታው በላሊና ተፅእኖ ውስጥ በመቆየቱ በሀምሌ ወር የነበረው ከፍተኛ የዝናብ መጠን በነሀሴ ወርም የሚቀጥል ሲሆን በመስከረም ወር ክረምቱ መውጣቱን ተከትሎ የሚኖረው የዝናብ መጠን እየቀነሰ እንደሚመጣ ጠቁመዋል። ቀጣዩ የዝናብ ወቅቶች ለግብርና፣ ለአካባቢ ጥበቃ እና የዝናብ ውሃን ለመያዝ ምቹ እድል እንደሚፈጥር ተገልጿል።

አብዛኛው የኦሮሚያ ክልል፣ አማራ፣ ትግራይ፣ደቡብ ምዕራብ ፣ድሬዳዋ፣ ሀረሪ፣ ጋምቤላ እና ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከፍተኛ የዝናብ መጠን የሚያገኙ ክልልሎች ናቸው።
ሆኖም ቀደም ብሎ ከፍተኛ የዝናብ መጠን ያገኙ የሀገሪቷ ክፍሎች አነስተኛ የዝናብ መጠን እንኳን ቢያገኙ የሚደርስባቸው ተፅዕኖ ከፍተኛ ሊሆን እንደሚችል ቅድመ ጥንቃቄ ሊደረጉ ይገባል ብሏል ኢንስቲትዩቱ።
በእርሻ መሬት ላይ የውሃ መተኛት፣ የመሬት መንሸራተት፣ የጎርፍ አደጋ፣ የአዋሽ ተፋሰስ፣ የጣና በለስ እና ፎገራ ባሉ ግድቦች ከመጠን በላይ የውሃ ሙሌት ሊያስተናግዱ በመቻላቸው ጥንቃቄዎች መደረግ እንዳለበት ተገልጿል።
ከየካቲት እስከ ግንቦት ባሉ የበልግ ወራት በኢትዮጵያ ያልተጠበቀ የዝናብ መከሰቱን ገልጸዋል። ይህም አየር ንብረቱ በአሊኖ ተፅእኖ ስር በመሆኑ በአብዛኛው የሀገሪቷ ክፍሎች ያልተጠቀ ዝናብ ሊከሰት መቻሉን አንስተዋል።
በ-ሀሴት ሀይሉ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












