፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 23 2016| NBC ETHIOPIA- በደቡባዊ ቻይና ባህር ስጋት የገባት አሜሪካ ከፊሊፒንስ ጋር ወታደራዊ ትብብር ለማድረግ ስምምነት ላይ መድረሷ ተገለፀ።
የማኒላ ባለስልጣናት እንደገለጹት ዋሽንግተን ለወታደራዊ እርዳታ የሚውል 500 መቶ ሚሊዮን ዶላር እገዛ ለማድረግ ቃል ገብተዋል ።
በኢንዶ ፓስፊክ ቀጠና የሚታየውን የቻይናን የበላይነት ለመከላከል ሲባል አሜሪካና አጋሮቿ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ውጥረቱን ያባብሰዋል እየተባለ ነው።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አንቶኒ ብሊንከን እና የመከላከያ ሚኒስትሩ ሎይድ ኦስቲን ከፊሊፒንስ ፕሬዚዳንት ፈርድናንድ ማርቆስ ጋር በነበራቸው ቆይታ ቻይና በፊሊፒንስ ላይ የምታደርገውን ወታደራዊ ትንኮሳ ማስቆም በሚቻልበት ሁኔታ ዙሪያ መክረዋል።
ከዚህ ጋር ተያይዞ የታይዋን ፕሬዝዳንት ላይ ቺንግ ቴ ቻይና ሀገራቸውን የምትወር ከሆነ ከዩክሬን- ሩሲያ ጦርነት እና ኮቭድ 19 በበለጠ፤ በዓለማችን ላይ ከባድ ነገር ይከሰታል ሲሉ አስጠንቅቀዋል ዘገባው የኢንዲፔንደንት ነው፡፡
በ- ቶማይ መኮንን
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












