፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 23 2016| NBC ETHIOPIA- በቬኔዙዌላ ሰሞኑን በተካሄደው ምርጫ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ኒኮላስ ማዱር የማሸነፋቸው ነገር ከሀገር ቤት እስከ በርካታ የውጭ መንግስት ሀገራት ድረስ ቀጠናዊ ተቃውሞ መቀስቀሱ ይታወቃል፡፡
በዚህ የተነሳ የቬኔዙዌላን ምርጫና ውጤቱን እውቅና አንሰጥም በሚል ተቃውሞአቸውን ካሰሙት ሀገራት ነው የቬኔዙዌላ መንግስት ዲፕሎማቶቿን ያስጠራችው፡፡
ሀገሪቱ ዲፕሎማቶቿን ካስጠራችባቸው ሀገራት መካከልም አርጀንቲና ፣ ዶሜኒካን ሪፐብኒክ ፣ ኮስታሪካ ፣ ፓናማ ፣ ፔሩ ፣ ኡራጓይ ና ቺሊ ተጠቃሹቹ ሆነዋል፡፡
የቬኔዙዌላ መንግስት ከዚሁ ጋር በተያያዘ መግለጫው ሀገራቱ በሉዓላዊነት ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ፈፅመውበናል ነው ያለው፡፡ ዘገባው የመኸር ኒውስ ነው፡፡
በ-ትዕግስቱ በቀለ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












