Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home News

ሰሞነኛ አስገራሚ ጉዳዮች

July 29, 2024
in News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

አለማችን በየእለቱ አስቂኝ፤ አሳዛኝ ብሎ አስገራሚ ሁነቶችን ታስተናግዳለች፤ እነዚህን ሁነቶች ደግሞ ሰብስቦ ለአለም እወቁልኝ የሚሉ ዘመን አመጣሽ የቴክኖሎጂ ወሬ ነጋሪዎች በርካታ ናቸው፡፡

ለዛሬ ከነዚህ የመረጃ ቋቶች ከሰበሰቧቸው ሳምንታዊ አስገራሚ ሁነቶች መካከል ጥቂቶቹን እንንገራችሁ፡፡

የ49 አመቷ ጎልማሳ አካል ጉዳተኛ በመምሰል ረብጣ ዶላሮችን ስትሰበስብ ነበር ሲል ኦዲቲ ሴንትራል አስነብቧል፡፡ ወደው አይስቁ!

ሳራ ሞሪስ የተባለችው ይህቺ እንግሊዛዊት ከግንቦት 2019 ጀምሮ እስከ 2022 ድረስ በሀገሪቱ መንቀሳቀስ ለማይችሉ አካል ጉዳተኞች የሚሰጠውን ወርሀዊ ድጋፍ እየተቀበለች በሀገሪቱ የተለያዩ ሩጫ መድረኮች ላይ ስትሳተፍ ነበር ይላል ዘገባው፡፡

ግለሰቧ ወደ ተቋሙ እርዳታን ለማግኘት ስትል ከአልጋ መንቀሳቀስ እንደማትችል፤ ያለእርዳታ መታጠብ መመገብ ሆነ ወደ መጸዳጅ ማቅናት እንደማትችል መድሀኒትም በሰው ድጋፍ እንደምትወስድ በመናገር በወር 2ሺ 292 ዩሮ እንዲሰጣት አድርጋለች፡፡ሳይሰሩ ገንዘብ ለማግኘት ሲባል በራስ ላይ እንዲህ ማሟረትን ምን ይታል?

የሌባ አይነ ደረቅ እንዲሉ ድጋፉን ሰትተዋት ዞር ባሉ ማግስት ለሩጫ ባላት ታላቅ ፍቅር በ5ሺ እና በ10ሺ ሜትር ኪሎ ሜትሮች ሩጫ በመሳተፍ በጥቅሉ ከ 73 ያላነሱ ውድድሮች ላይ በነዚህ አመታት ተሳትፋለች፡፡

ይህ ሁሉ ሁነት ሲሆን አንዳችም ሰው ያልነቃባት ሳራ በአንድ የሩጫ ውድድር ላይ ሳለች የሚያሳይ ምስል በፌስቡክ ትስስር ገፅ መለቀቁን ተከትሎ የእስከዛሬ ድርጊቷ እንዲታወቅባት ሆኗል፡፡

ወትሮውንም ለሩጫ ያላትን ፍቅር የማትደብቀው ሳራ እስከዛሬ እያጭበረበረች ትቀበል እንደነበር አምናለች፤ ድርጅቱም ሁነቱን በመቃወም በነዚህ ሁሉ አመታት አንድ እርምጃ መሄድ እንኳን የማይችልን ሰው ጥቅም በማታለል ስታገኝ ነበር ሲል ከሷታል፡፡

ሌላኛው አስገራሚ መረጃችን ደግሞ በሩሲያ ለዘጠኝ አመታት በህመም ሲሰቃይ የነበረ ግለሰብ በመጨረሻም የህመሙ ምክንያት ታወቀለት ይለናል፡፡ስሙ ያልተገለጸው የ53 አመቱ ሩሲያዊ ባለፉት ዘጠኝ አመታት በቀኝ ደረቱ አካባቢ የመውጋት አንዳንዴም ከፍተኛ ህመም ቢሰቃይም ወደ ህክምና ተቋም ሄዶ ለመመርመር አስቦ አያውቅም ነበር ተብሏል፡፡

ግለሰቡ ህመሙ ሲበረታበት በአንድ እለት ወደ ሆስፒታል በማቅናት በታዘዘለት የሲቲስካን ምርመራ በጉበቱ ቀኝ ክፍል የተጣበቀ ስለታም ነገር እንደሚታይ በመግለጽ ዶክተሮቹ ምን ሊሆን እንደሚችል ቢጠይቁትም ፈፅሞ ሊያውቅ እንደማይችል ተናግሯል፡፡

በመጨረሻም በተደረገለት ቀዶ ህክምና በጉበቱ ቀኝ ክፍል 9ሴንቲ ሜትር የሚረዝም የመስታውት ቁራጭ ሊያስወግዱለት ችለዋል፡፡

ትረፊ ያለት ነፍስ እንዲሉ ከ9አመታት በኋላ የህመሙ ምክንያት ስለመገኘቱ ከወጣለት የጠርሙስ ቁራጭ ጋር በማድረግ በማህበራዊ ሚዲያ በማጋራት በበርካቶች አነጋጋሪ ሆኗል፡፡

አልበላም አልጠጣም ብዬ እንዲል የሀገሬ ሰው ጃፓናዊው ግለሰብ አልበላም አልጠጣም በማለት ላለፉት 21 አመታታ ያጠራቀምኩት ገንዘብ በ45 አመቴ ጡረታ እንድወጣ ረድቶኛል ይለናል፡፡

ግለሰቡ ባለፉት 2 አስርት አመታት ፍላጎቶቹን ፍጹም ገድቦ 130 ሚሊየን የን ወይንም 640ሺ ዶላር ማጠራቀሙ በማህበራዊ ሚዲያዎች የበርካቶች መነጋገሪያ ሆኗል፡፡

 FIRE (Financial Independence, Retire Early) ወይንም የገንዘብ ነጻነትን በጊዜ በማስፈን ጡረታ መውጣት በውጪ ሀገራት በይበልጥ እየተለመደ የመጣ ሁነት ሲሆን የዚህን ግለሰብ ድርጊት ለየት ያደረገው 21 አመታት መሰረታዊ ፍላጎቶቹን ሁሉ ገድቦ መኖሩ ነው፡፡

በየአመቱ ከ32ሺ በላይ ዶላር ደሞዝ ያግኝ እንጂ በቀን 1ጊዜ የተቀቀለ ሩዝ እና እራቱን ለስላሳ መጠጥ በመጠጣት ገንዘብ ማጠራቀሙ ተነግሯል፡፡

ግለሰቡ ርካሽ ልብሶች እና ጫማዎችን በመጫማት፤ ለመዝናናት ደግሞ የቴሌቪዥን ወንጀል ፕሮግራሞችን በመመልከት ፤ ይባስ ብሎ ደግሞ በክረምት ወቅቶች እንኳን በቤቴ ማሞቂያ ሳይኖር ነው ያሳለፍኩት ሲል ይገልጻል፡፡ የርሱን ጽሁፍ በማህበራዊ ሚዲያ የተመለከቱ ሁሉ ላይ ግርምትን ጭሯል፡፡ አልሞት ባይ ተጋዳይ ማለት እዲህ ያለውን ነው፡፡ ነገን አስቦ ዛሬ አለመኖር

በ-የአብስራ ሚሊዮን

ShareTweetShare
Previous Post

የዕፅ አዛዋዋሪዎቹ በቁጥጥር ስር ዋሉ

Next Post

በሲዳማ ክልል በደረሰ የመሬት መንሸራተት 6 ሰዎች ህይወት አለፈ

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
9
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
8
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
16
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
52
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
38
Next Post
በሲዳማ ክልል በደረሰ የመሬት መንሸራተት 6 ሰዎች ህይወት አለፈ

በሲዳማ ክልል በደረሰ የመሬት መንሸራተት 6 ሰዎች ህይወት አለፈ

ወጣቶች የትራንስፖርት አገልግሎቶችን ለማሻሻል ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ተገለፀ

ወጣቶች የትራንስፖርት አገልግሎቶችን ለማሻሻል ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ተገለፀ

የቱርክ ማስፈራሪያ በእስራስኤል ላይ

የቱርክ ማስፈራሪያ በእስራስኤል ላይ

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?