፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 22 2016| NBC ETHIOPIA- በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ወንሾ ወረዳ ግሽሬ፤ጉዱሞና ሆሞ ትናንት በጣለው ከፍተኛ ዝናብ ምክንያት መሬት በመንሸራተቱ የስድስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ስድስት ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱ ተገልጿል፡፡
ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖች የሕክምና ዕርዳታ እያገኙ መሆኑን የገለጸው የክልሉ መንግሥት፤ ተጨማሪ ድጋፍ ለማድረግ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን እና የጸጥታ አካላት ወደ ስፍራው ማቅናታቸውን አስታውቋል፡፡
በሌሎች አካባቢዎችም መሰል ችግሮች ሊፈጠሩ ስለሚችሉ ሕብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ማሰሰቡን ከሲዳማ ክልል ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ይመለክታል፡፡ ኤንቤሲ ኢትዮጵያ በአደጋው ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች፣ወዳጆችና ዘመዶች መጽናናትን ይመኛል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












