፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 19 2016| NBC ETHIOPIA- በዓለም ከሚገኙ ዋና የአደንዛዥ ዕፅ አዘዋዋሪዎች አንዱ የሆነው ሜክሲኳዊው ኢስማኢል ኤል ማዮ ዛምባዳ ከኤል ቻፖ ልጅ ዮዋኪን ጉዝማን ሎፔዝ ጋር በአሜሪካ ቴክሳስ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተገለጸ፡፡
ሁለቱ የ70 እና 30 ዓመት አደጋኛ ዕፅ አዘዋዋሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የአሜሪካ ፍትሕ ሚኒስትር በመግለጫው አስታውቋል።
ዛምባዳ ፌንታኒል የተሰኘ አደገኛ ዕፅ በማምረትና በማዘዋወር ወንጀል ተከሶ እንደነበር እና አመፀኛ ከሚባሉ የዕፅ አዘዋዋሪ ድርጅቶች ውስጥ አንዱን እንደሚመራ የአሜሪካ አቃቤ ሕግ ገልጿል።
ከሄሮይን የበለጠ ኃይል እንዳለው የሚነገርልት ፌንታኒል አሜሪካ ውስጥ ወጣቶችን ለብዙ ማህበራዊ ቀውስ እንደሚዳርግና ዕድሜያቸው ከ18-45 ባሉ አሜሪካዊያንን ዘንድ ቁጥር አንድ የሞት መንስዔ እንደሆነ መረጃዎች አመላክተዋል፡፡ ዘገባው የአልጀዚራ ነው
በ-ቶማይ መኮንን
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
Facebook –https://www.facebook.com/ethiopiannbc












