Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home News

ካማላ ሃሪስ ማን ናቸው…?

July 23, 2024
in News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

ካማላ ሃሪስ ማን ናቸው…?

በልጅነት አእምሯቸው ሲሰሙ ያደጉት የአያታቸው የታጋይነት ታሪክ አሁናዊ ማንነታቸው ላይ አዎንታዊ ተፅዕኖ እንዳሳደረባቸው ይነገራል፡፡ ህንዳዊቷ እና ጀማይካዊቷ የአሜሪካ ቁልፍ ዴሞክራት ፖለቲከኛ ሰፊ የማንነት ልዩነት ካላቸው ቤተሰቦች ዝርያቸው ይመዘዛል ፡፡

በአሜሪካን ታሪክ የመጀመሪያ ጥቁር አሜሪካዊ እና እስያ አሜሪካዊት ሴት ምክትል ፕሬዚዳንት ናቸው ካማላ ዴቪ ሃሪስ፡፡በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1964 ወርሃ ጥቅምት በኦክላንድ ካፎርኒያ ነው የተወለዱት ከህንዳዊ እናታቸው Shyamala Gopalan እና ጃማይካዊ አባታቸው Donald J. Harris የተገኙት ካማላ ለቤተሰባቸው የመጀመሪያ ልጅም ናቸው፤ወላጅ እናታቸው ባይሎጂስት እና የሰብአዊ መብት ተሟጋች ሲሆኑ ወላጅ አባታቸው በስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሀብት ባለሞያ እና ፕሮፌሰር እንደነበሩ የህይወት ታሪካቸው ያትታል፡፡

ካማላ የሚለው ስያሜያቸውን ያገኙት የሂንዱ እምነት ተከታይ ከሆኑት እናታቸው ሲሆን ስያሜው በሂንዱ እምነት የምትመለከውን እና ብዙ ሴቶች አቅማቸውን እንዲገነቡ ታደርጋለች ብለው ከሚያስቧት  ላኪሽ የተሰኘችው ሴት አማልክት የመጣ እንደሆነም ይነገራል፡፡
የሰባት አመት ታዳጊ ሳሉ ወላጆቻቸው በፍቺ መለያየታቸውን ተከትሎ ካማላ እና ታናሽ እህታው ማያ ከወላጅ እናታቸው ጋር  ለማደግ ተገደዋል፡፡በልጅነታቸው ጥቁር አሜሪካውያን በቆዳ ቀለማቸው የሚደርስባቸው ግፍ ጭቆና በተወሰነ መጠን   በአንድ ወቅት  ሰለባ ነበሩ፡፡
ካማላ ሃሪስ ከካሊፎርኒያ የህግ ኮሌጅ የህግ ዲግሪ ከማግኘታቸው አስቀድሞ በዋሺንግተን ዲሲ በሚገኘው ሃዋርድ ዩኒቨርሲቲ ምሩቅም ናቸው፡፡
እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1990 በተማሩበት የህግ ሞያ የጥብቅና ስራቸውን የጀመሩት ካማላ 2003 የሳን ፍራንሲስኮ  አቃቤ ህግ ሆነው አገልግለዋል፡፡ካማላ ሃሪስ ስራቸውን  የጀመሩትም የህጻናት እና በቤት ውስጥ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን የህግ ጉዳዮ  በመያዝ  ነበር፡፡
በ2010 በካሊፎርኒያ ግዛት ጠቅላይ አቃቤ ህግ በመሆን ያገለገሉ ሲሆን ከ4 አመታት በኋላም ዳግም ተመርጠው በግዛቱ ከፍተኛ የህግ አስፈፃሚ ቦታም ያገለገሉ የመጀመሪያዋ ጥቁር ሴት መሆን ችለዋል፡፡
በፈረንጆቹ 2016 በአሜሪካ ምክር ቤት አባልነት የተመረጡት ካማላ ሃሪስ የዶናልድ ትራምፕ የስደተኞች ፖሊሲ ላይ ጠንከር ባለ ትችት ሲሰነዝሩም ይታወቃሉ፡፡ በተለይም በ2018 የአሜሪካ የጠቅላይ ፍርድቤት እጩ የነበሩትን ብሪት ካቫንጉሀን ጠንከር ባሉ ጥያቄዎቿ  መተንፈሻ አሳጥታዋቸው ነበር፡፡  በሳል ፖለቲከኛ  እና የዲሞክራቶች ቁልፍ ልጅ መሆናቸውን በአባሎቻቸው እና በህዝብ ፊት አስመስክረዋል፡፡
ካማላ ሃሪስ በአቃቢነት ዘመናቸው ከነበረው የፍቅር ጓደኛቸው ዊሊያም ብራውን በመቀጠል በ2014 በስራ አጋጣሚ የተዋወቁትን ጠበቃ ዳግላስ ኤም ሆፍ ጋር በትዳር በመጣመር የባለቤታቸውን 2 ልጆች በጋራ ያሳድጋሉ እንጅ የአብራክ ክፋይ የላቸውም፡፡
ሃሪስ በ2020ው የአሜሪካ ምርጫ እጩ የነበሩ ሲሆን ነገር ግን በመጀመሪያው ዙር የውድድር ሂደት ላይ እምብዛም የክርክር አፈፃፀሞችን ካሳዩ በኋላ በፍጥነት ደበዘዘዋል፡፡ ዴሞክራቶችን መወከል አልቻሉም ነበር፡፡በተመሳሳይ የምርጫ ዘመን ላይ ለፕሬዘዳንት ሲፎካከሩ የነበሩት ጆ ባይደን ለእርሳቸው የምርጫ ሂደት ሴት የስራ አጋር እንደሚያስፈልጋቸው በመግለፅ ካማላ ሃሪስ ወደፊት እንዲመጡም ሆነዋል፡፡
የእርሳቸው ወደፊት መምጣት ጆባይደን የጥቁር አሜሪካውያንን እንዲሁም የሴት መብት ታጋዮችን ትኩረት ይበልጥ እንዲስቡ  እና ስልጣነ መንበሩን እንዲቆናጠጡም በብዙ ደግፏቸዋል፡፡ ወደ ነጩ ቤተመንግስት በመግባት የመጀመሪያዋ ጥቁር አሜሪካዊት ሴት፤እንዲሁም እስያዊ ምክትል ፕሬዚዳንት በመሆን የመጀመሪያዋ የሚሉ ማዕረጎችን የማግኘት ታሪክ ሰርተዋል፡፡
ባለፉት 4 አመታት የምክትል ፕሬዘዳንትነት ቆይታቸውን ሃሪስ ደካማ የሚባል ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ አሳይቷል የሚሉ በአንድ ወገን  በሌላ ወገን ለብዙ ጥቁር ሴት ፖለቲከኞች መነሳሳት ምክንያት ሆነዋል በሚል በርካቶችን ያከራክራሉ፡፡ የስደተኞች ፖሊሲ ፤ የጦር መሳሪያ ቁጥጥር እና ከውርጃ መብት ጋር ተያይዞ ሰፊ እንቅስቃሴ በማድረጋቸውም ትችቱን ውድቅ የሚያደርጉትም አሉ፡፡
ለሁለተኛ ዙር የስልጣን ዘመን እየወደቁ እና እየተነሱ የአልሞት ባይ ተጋዳይነት ፉክክር ሲሳዩ የከረሙት ፕሬዘዳነት ጆባይደን ከምርጫው እራሳቸውን ማግለላቸውን ተከትሎ ካማላ ሃሪስ ዴሞክራቶችን ወክለው ለፕሬዝዳንትነት ትራምፕን ለመግጠም ታጭተዋል፡፡ ምናልባት ሃሪስ የብሄራዊ ጉባዔውን ሙሉ ድጋፍ ካገኙ በህዳር 5ቱ ምርጫ ላይ ከሪፐብሊካኖቹ ጋር ይፋጠጣሉ ተብሎ ይጠበቃል ፡፡
ሃሪስ እድሉን ካገኙ ከዶናልድ ትራምፕ ጋር በሚኖራቸው የምርጫ ፉክክር ምን ይገጥማቸዋል የሚለውም መነጋገሪያ እየሆነ መጥቷል ፡፡ዶናልድ ትራምፕም በበኩላቸው የጆባደንን ከምርጫ ራስን ማግለላቸውን እና ካማላ መተካታቸው አሁን ይበልጥ ቀለለኝ አይነት ፌዝ ማሰማታቸው እያነጋገረም ይገኛል፡፡
እርሱም ሳያንስ የ59ኝ አመቷ ካማላ ሃሪስን ከዚህ ቀደም ባደረጉት የመድረክ ንግግሮች ላይ ወደ መድረክ ከመውጣታቸው አስቀድሞ ወይን ይቀማምሳሉ በዚህም በርካታ ጊዜ ትርጉም አልባ ወሬ ሲያወሩ ተስተውለዋል ያሉባቸው አጋጣሚዎች መለስ ብለው ዳግም እያስቃኙ ይገኛሉ፡፡
ነገር ግን ህንድ ከእንግሊዝ ቀኝ ግዛት ለመላቀቅ የፈጸሙትን የአያታቸውን የተጋድሎ ታሪክ እየሰሙ ያደጉት እና የታጋይነት መንፈስ በሰፊው የሚስተዋልባቸው፤ ጥቁርነታቸው፣ ሴትነታቸው ሳያግዳቸው የመጀመሪያዋ የሚሉ በርካታ ማዕረጎችን ማሳካት የቻሉ ካማላ ሃሪስ የመጀመሪያዋ ጥቁር እስያዊ አሜሪካዊ ሴት ፕሬዘዳንት ለመሆን ያዳግታቸው ይሆን የመጪው ህዳር ወር ምላሹን ይዞ ይመጣል፡፡ ሃሪስ ነሀሴ 19 የሚደረገውን ጉባኤ ተከትሎ የዴሞክራቶቹን ሙሉ ድጋፍ አግኝተው ወደ ውድድሩ መድርክ ከመጡ እንደማለት ነው፡፡
 በ-የአብስራ ሚሊዮን
ShareTweetShare
Previous Post

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር የአሜሪካ ጉብኝት

Next Post

የብልጽግና ፓርቲ የሐዘን መግለጫ

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
9
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
8
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
16
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
52
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
38
Next Post
የብልጽግና ፓርቲ የሐዘን መግለጫ

የብልጽግና ፓርቲ የሐዘን መግለጫ

ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ስልጣናቸውን እንዲለቁ እየተጠየቁ ነው

ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ስልጣናቸውን እንዲለቁ እየተጠየቁ ነው

በአውሮፓ ከፍተኛው ሞቃታማ ቀን ተመዘገበ

በአውሮፓ ከፍተኛው ሞቃታማ ቀን ተመዘገበ

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?