፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 16 2016| NBC ETHIOPIA-የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር በቀጣዩ ሀሙስ ከአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጋር እንደሚገናኙ ተገልጿል፡፡
የአሜሪካ ባለስልጣናት በሰጡት ማብራሪያ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ጋር ከነገ በስተያ ሀሙስ ዕለት በኃይት ሀውስ ተገኝተው እንደሚመክሩ አስታውቀዋል፡፡
ከባለፈው ረቡዕ ጀምሮ በኮቪድ-19 መያዛቸው የተሰማው ጆ ባይደን ዛሬ ከዴልዌር ይመለሱና ዋሽንግተን ይገባሉ ነው የተባለው፡፡
ወደ አሜሪካ የተጏዙት የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔትንያሁ ከባይደን ጋር በሚያደርጉት ምክክር በጋዛ ሰርጥ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ በሚደርሱበት መንገድ ዙሪያ ይመክራሉ ተብሎም ይጠበቃል፡፡
ባይዳን በሀገሪቱ በሚካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እንደማይፎካከሩ ካስታወቁ በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከውጭ ሀገር መሪ ጋር የሚያደርጉት ውይይት መሆኑን የኢንቨስቲግ ኮም ዘገባ ያስረዳል፡፡
በ-ትዕግስቱ በቀለ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv

See insights and ads
Like
Comment
Send
Share












