፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 152016| NBC ETHIOPIA-የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ዘለንስኪ ከሩሲያ ጋር የሰላም ስምምነት ለማድረግ የሚፈልጉ ከሆነ ፤ በቅድሚያ ህዝበ ውሳኔ ማድረግ አለባቸው ሲሉ የኬይቭ ከንቲባ ቪታሊ ክሊቲሽኮ አስጠነቀቁ፡፡
የትኛውም የፕሬዝዳንት ዘለንስኪ እንቅስቃሴ የፖለቲካ ኪሳራ የተጋረጠበት ወደመሆን እየተቃረበ እንደሚገኝ ነው ከንቲባው ያመላከቱት፡፡፡
እሁድ ዕለት ጣሊያን ከሚገኝ ሚዲያ ጋር ቆይታ ያደረጉት ከንቲባው የሚቀጥሉት ጥቂት ወራት ለፕሬዝዳንት ዘለንስኪ እጅግ ፈታኝ ናቸው ብለዋል፡፡
አሁን እየጠበቅን ያለነው የአሜሪካን ምርጫ መጠናቀቅ ሲሆን ነገር ግን ከሞስኮ ጋር የሰላም ድርድር ለማድረግ ሁሉም ሰው የሚሳተፍበት ህጋዊ ህዝበ ውሳኔ አስፈላጊ ነው ፡፡ አክለውም ዘለንስኪ ያለህዝብ ፍቃድ ብቻቸውን ይህንን አደጋኛ ውሳኔ እንደማይወስኑ ይሰማኛል ሲሉ ገልጸዋል ፡፡ የፕሬዝዳንት ቭላድሚር ዘለንስኪ የስልጣን ቆይታ ጊዜያቸው ባለፈው በፈረንጆቹ ግንቦት 2024 አልቆ የነበረ ቢሆንም አሁን ባለው የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ምክንያት ምርጫ ማድረግ አልፈለጉም ተብሏል፡፡
ስለሆነም ብቻቸውን የሰላም ድርድር የማድረግ ስልጣን የላቸውም የሚሉ ወገኖች መበራከታቸውን የዘገበው አር ቲ ኒውስ ነው፡፡
በ-ቶማይ መኮንን
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












