፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 152016| NBC ETHIOPIA- ሩሲያ ሁለት የዩክሬን መንደሮችን መያዟ ተነግሯል። የሩሲያ የመከላከያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ በዩክሬን በገባበት ጦርነት በሉሃንስክ ግዛት ሁለት ተጨማሪ መንደሮችን መያዙን አስታውቋል።
ዜናውን ያሰራጩት የታስ እና ሬውተርስ የዜና ምንጮች ሲሆኑ ስለወጣው መረጃ ግን እስካሁን ከገለልተኛ ወገን አልተጣራም ነው የተባለው በጉዳዩ ዙሪያ ከዩክሬን ባለስልጣናትም የተሰጠ ምላሽ የለም።
የሩሲያ የመከላከያ ሚኒስቴር በዕለታዊው መግለጫው የጦር ሀይሉ ሁለት ተጨማሪ መንደሮችን መቆጣጠሩን ነው ያስታወቀው የሩሲያ ጦር ሀይል እነዚያን ሁለት መንደሮች መቆጣጠሩ ቢነገርም የሰብዓዊ እና ቁሳዊ ኪሳራው ከባድ እንደነበረ የኖቪንቴ ኮም ዘገባ ያስረዳል።
በ-ትዕግስቱ በቀለ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












