፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 12 2016| NBC ETHIOPIA-ዩክሬን በሩሲያ ውስጠኛ ክፍል ዘልቃ ጥቃት እንድትፈፅም የእንግሊዝ መንግስት ይደግፋት ዘንድ ጠይቃለች።
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቨሎዲሚር ዘለንስኪ የእንግሊዝ አዲሱ መንግስት የዩክሬን ሀይሎች በታጠቋቸው እና ከምዕራባውያን ባገኟቸው የረዥም ርቀት ተምዘግዛጊ የጦር መሳሪያዎች የሩሲያን ውስጠኛ ክፍል በተገቢው ይመቱ ዘንድ ፈቃድ እንዲሰጧቸው ነው ብርቱ ጥያቄያቸውን ያቀረቡት።

እንደ ዘለንስኪ ጥያቄ በዚህ ወቅት የረዥም ተምዘግዛጊ ሚሳይሎች የሩሲያ የጦር መሣሪያ ማከማች ስፍራዎች እና የዕዝ ስፍራዎች ለማውደም ተመራጮች ናቸውና መጠቀም አለብን ነው ያሉት ዘገባው የዋሺንግተን ታይምስ ነው።
በ-ትዕግስቱ በቀለ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












