፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 10 2016| NBC ETHIOPIA-የክልሎች አጀንዳ ማሰባሰቢያ መርሃግብር ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ እንደሚከናወን ተገለጸ፡፡
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በቤንሻጉል ጉሙዝ፣ድሬደዋ፣ሀረር፣እንዲሁም ጋምቤላ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰቢያ መርሃግብር ቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተጠናቀው በቀጣይ ሳምንት እንደሚጀምር ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን ዓርዓያ በክልል የሚከናወነው የአጀንዳ ማሰባሰብ መርሃግብር እስከ ነሀሴ 30 በአብዛኛው ክልል እንደሚከናወን በማንሳት በአማራና ትግራይ ክልል ግን በርካታ ስራዎች እንደሚቀሩ ተናግረዋል።ሀገራዊ ምክክር እውን እንዲሆን ሁሉንም የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል።
በ-ሰላም ይልማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












