፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 09 2016| NBC ETHIOPIA- እስራኤል ጦሯን ግብፅና ጋዛ በሚዋሰኑበት ድንበር ይቆይ ዘንድ መወሰኗ ተነግሯል፡፡
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በሠጡት ማብራርያ የሀገሪቱ ጦር ሀይል በግብፅና በጋዛ ሰርጥ የመዋሠኛ ድንበር የፊላደልፊ ኮሪደር እንዲቆይ ትዕዛዝ መስጠታቸው ነው የተሰማው፡፡

ኔታንያሁን በመቃወም የሚታወቁት የእስራኤሉ የመከላከያ ሚኒስትር የአቭ ጋላንት በበኩላቸው በጉዳዩ ዙሪያ ያሉት ነገር ባይሰማም በኔታንያሁ አቋም ሳይስማሙ እንደማይቀር ነው የተነገረው፡፡ ይኸው የእስራኤል ጦር ሀይል በፊላደልፊ ኮሪደር የመቆየት ነገር በሀገሪቱ ካቤኔ ውሳኔም እንደሚጠበቀውም ነው የተገለፀው፡፡ዘገባው የአናዶሉ ነው፡፡
በ-ትዕግስቱ በቀለ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv











