Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home Health

የሙቀት መጠን መጨመር ተፅዕኖ በነፍሰጡር እናቶች

July 16, 2024
in Health, News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ 

አዲስ አበባ | ሐምሌ 09 2016| NBC ETHIOPIA-የአየር ንብረት በነፍሰ-ጡር እናቶች ላይ ተፅዕኖ እየጎላ መምጣቱን ያስነበበው ቢቢሲ በተለይ እየጨመረ የመጣው የሙቀት መጠን በእርግዝና ወቅት በጽንስ ላይ ሊያስከትል የሚችለው ጉዳት አደገኛ ነው ይላል፡፡ ይህም የነብሰ-ጡር እናቶችን ህይወት በአስጊ ሁኔታ ላይ እንዲቆይ አድርጓል፡፡
ቢቢሲ በሰራው ዘገባ በጋምቢያ ኬኔባ በምትሰኘው የገጠር መንደር ላይ ያለን የእናቶች ስቃይ ፍንትው አድርጎ አሳይቷል፡፡ ኤድሪሳ ሲንጃንካ በመንደሩ በአዋላጅነት እየሰራ የሚገኝ ሀኪም ነው፣ እርሱ ነፍሰጡር እናቶችን ማገዝ ያስ ደስተኛል ይላል፡፡ ነገር ግን እናቶች ወደ እኔ ሲመጡ ከንፈራቸው ደርቆ እና ተሰንጥቆ ፤ራስ ምታት በከፍተኛ መጠን ሲፈትናቸው ማየቴ የተለመደ ነው ይላል፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከሙቀት መጠን መጨመር ጋር ተያይዞ በነብሰ-ጡር እናቶች ላይ እያጋጠመ ያለውን የጤና እክልን ይናገራል፣ እርሱ እንደሚለው እናቶች የእርግዝና ወቅታቸው አስቸጋሪ እየሆነ መጥቷል፡፡ አንዳንድ ሴቶች በምጥ ወቅት እየተቸገሩም ነው፡፡በወሊድ ምክንያት ህይወታወቸውን የሚያጡ እናቶች እየተበራከቱ መሆናቸውም ተመላክቷል፡፡

በጋምቢያ የታየው ሙቀት መጨመር በዚች የገጠር መንደር የሚገኙ እናቶች በእርግዝና ወቅት ከፍተኛ ስጋት እንዲደቀንባቸው አድርጓል፡፡በኬኔባ አካባቢ 92 ነፍሰ-ጡር እናቶች ላይ በተሰራ ጥናት የዕለት ተዕለት ተግባራቸውን ሲያከናውኑ በየሁለት ወሩ አንድ ጊዜ በሚከሰት የሙቀት መጠን መጨናነቅ ታይቶባቸዋል፡፡

ከመደበኛ በላይ የሆነው የሙቀት መጠን ጭንቀት፣ የልብ ምት መጨመር እንዲሁም የእንግዴ ልጅ የደም መፍሰስ መጠን በ17 በመቶ ጭማሪ እንዲያሳይ አድርጓል፡፡ አንድ ሦስተኛ የሚሆኑእናቶች በዚህ ችግር ውስጥ መሆናቸው መረጃው ያመላክታል፡፡በጋምቢያ፣ የሙቀት መጠኑ ከ45C ተሻግሯል፡፡

በተለይ ከ2023 ጀምሮ ዓለምን እያስጨነቀ የመጣው የዓለም ሙቀት መጠን መቆጣጠር ላይ ካልተሰራ በህጻናት፣ አዛውንቶች ፣ እና ስር በሰደደ የጤና ችግር ውስጥ በሚገኙ ሰዎች ብሎም ነፍሰጡሩ እናቶች ላይ አደጋ ተጋርጦባቸዋል፡፡

በእርግዝና ወቅት የሆርሞን ለውጦች እና የቆዳው መለጠጥ ወይም መስፋት  እናቶች ይበልጥ ለሙቀት ተጋላጭ እንዲሆኑ ያደርጋል፡፡

በሙቀት የተፈተኑ ነፍሰጡር እናቶች የመውለጃ ቀናቸው ሲቃረብ ለልብ ሕመም፣ ለደም ግፊት፤ ለስኳር በሽታ እንዲሁም እስከ ሞት የሚያደርስ ስጋት ተደቅኖባቸዋል፡፡ችግሩን ለመቋቋም ቀለል ያሉ አልባሳትን መጠቀም ፣የአካል፣ የስሜት እና ማህበራዊ ጫናዎች ተጋላጭ የሚሆኑበት ሁኔታ መቀነስ፤ ጤናማ አመጋገብ እንዲከተሉ ማድረግ ማለትም ፍራፍሬና አትክልት ማዘውተር፤ በቂ ውሃን  መጠጣት፣ የአየር ማቀዝቀዣ መጠቀም፣ የሰውነት እብጠት እንዳይፈጠር ማድረግ እንዲሁም በእርግዝና ወቅት የሚመከሩ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማከናወን እንደመፍትሄ የሚቀመጡ ናቸው፡፡

በርካታ ሀገራት የሙቀት መጠን መጨመር የሚያሳድረውን ጫና ለመቀነስ ቢሰሩም ለነፍሰጡር እናቶች የሚደረጉት ድጋፍ አናሳ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡የአየር ንብረት ለውጥ ላይ ቃል ከገቡ 119 ሀገራት  20 በመቶ  የሚሆኑት ብቻ  የእናቶችን እና የፅንስ ጤናን በተመለከተ በእቅዳቸው ማስቀመጣቸውን  የተባበሩት መንግስታት የስነ-ተዋልዶ ጤና መረጃ አረጋግጧል፡፡

ጭራሽ ደግሞ በአፍሪካ የሚገኙ እናቶች በከባድ የመተዳደሪያ ስራዎች የተሰማሩ መሆናቸው እና ከሙቀት መጠን መጨመር ጋር ተያይዞ ችግሩን ለመዋጋት አዳጋች እንዳደረገው ይነሳል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ እንደሚያሳየው በሙቀት መጨመር በፈረንጆቹ 2024 ያለጊዜያቸው የሚወለዱ ህፃናት 16 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል ይላል፡፡ከፍተኛ የፅንስ መጨንገፍ እና ከወሊድ ጋር የተገናኘ የሞት አደጋም ተባብሶ ቀጥሏል፡፡

ነፍሰ-ጡር እናቶች በተለይ በአፍሪካ የሙቀት መጨመር ለሚፈጥረው ጭንቀት ተጋላጭ ሲሆኑ ችግሩን ለመቋቋም  አዳጋች የሚያደርገው እናቶች በከባድ ስራዎች ተሳታፊ መሆናቸው ነው፡፡ስለዚህም የትዳር አጋሮቻቸውን ጨምሮ በዙሪያቸው የሚገኙ ቤተሰቦቻቸው ጫናቸውን ሊያቃልሉ እንደሚገባ ተመላክቷል፡፡

የሙቀት መጨመር በፅንስ እድገት እና አዲስ በሚወለዱ ህፃናት ላይ ሊያስከትል  የሚችለውን አደጋ በጋምቢያ የተሰራው ጥናት ፍንትው አድርጎ ያሳያል፡፡

በበለጸጉ ሀገራት ነፍሰ-ጡሩ እናቶች ለሙቀት ተጋላጭ ቢሆኑም የህክማናን ክትትል በማድረግ እና ተገቢውን እንክብካቤ ስለሚደረግላቸው የተሻለ ውጤት እንዳለው ይነገራል፡፡  የዓለም ሙቀት መጨመር በነፍሰጥሮች ላይ የሚያሳድረው ጫና ቀላል ባለመሆኑ ይበልጥ አትኩሮት ይስፈልጋል ይላል ቢቢሲ፡፡

ShareTweetShare
Previous Post

የሩዋንዳን ምርጫ ለ አራተኛ ጊዜ ያሸነፉት ፖል ካጋሜ

Next Post

ኢንጂነር ታከለ ኡማ በንቲ የኢትዮ ጂቡቲ ባቡር አ.ማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተሾሙ

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
9
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
8
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
16
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
52
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
38
Next Post
ኢንጂነር ታከለ ኡማ በንቲ የኢትዮ ጂቡቲ ባቡር አ.ማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተሾሙ

ኢንጂነር ታከለ ኡማ በንቲ የኢትዮ ጂቡቲ ባቡር አ.ማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተሾሙ

በበርካታ መስህቦች የታደለችው ሀገር-ስፔን

በበርካታ መስህቦች የታደለችው ሀገር-ስፔን

ኢራን ትራምፕን ለመግደል እቅድ እንደነበራት ተገልጿል

ኢራን ትራምፕን ለመግደል እቅድ እንደነበራት ተገልጿል

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?