፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 04 2016| NBC ETHIOPIA-የጤና ሚኒስቴር የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ወደ ህብረተሰቡ ሲወርዱ የጤና ዘርፍ ስራዎችን ለመስራት እንዲያስችላቸው በጤናው ዘርፍ በሚሰሩ አጠቃላይ ስራዎች ላይ ገለጻ ተደርጓል።

በመድረኩ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ም/አፈ ጉባኤን ጨምሮ የምክር ቤት አባላት፣ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ፣ ሚኒስትር ዴኤታዎች ፣ የተጠሪ ተቋማት መ/ቤት ሃላፊዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እየተሳተፋ ነው።
በጤናው ዘርፍ ትኩረት ከሚሹ ዋና ዋና ጉዳዮች እና መሰረታዊ የጤና አገልግሎቶችን ጨምሮ የምክር ቤት አባላት ሚና እና የሚጠበቁ ድጋፎችን በተመለከተ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ ገለጻ አድርገው ውይይት እየተካሄደ ነው።
በ-ሰብለ ወንድማገኝ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












