፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሰኔ 28 2016| NBC ETHIOPIA-በፈጣን እድገት ላይ የሚገኘው አርቴፊሻል ኢንተለጄንስ ለበርካታ የቴክኖለጂዎች ውጤቶች ፈተና መሆኑን ቀጥሏል ተባለ፡፡ በdotcom bubble የሚመራውም የአሜሪካ የአክሲዮን ገበያም በአርቴሺሻል ኢንተለጀንስ እየተፈነ መሆኑ የሮይተርስ ዘገባ ያመላክታል፡፡
ዶት-ኮም በብል የስቶክ ገበያውን ለረጅም ጊዜ ተቆጣጥሮ የቆየ ነው፡፡የኢንተርኔት መንሰራፋትንም ተከትሎ ስራውን ማቀላጠፍ የቻለ ኩባንያ ነበር፡፡ ኩባንያው የኦላይን ሽያጭ ማከናውን እንዲሁም የአክሲዮን ገበያ በመቆጣጠር ረገድ ስሙ የናኘ ነው፡፡
ዶት-ኮም በብል ከ1990ዎቹ መገባደጃ ወዲህ በአሜሪካ ሌሎች ኩባንያዎችም በአክሲዮን ገበያው እዲቀላቀሉ በማስቻል ፍትሃዊ እና አማራጭ የአክሲዮን ገበያ እዲኖር ማስቻሉ ይነገርለታል፡፡ከሁለት አስርት አመታት በላይ በአክሲዮን ገበያው ትልቅ ሚና የተጫወተው ኩባንያው አሁን ላይ ከአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ እድገት ጋር ተያይዞ በሀገሪቱ ያለውን ተፈላጊነት እንዳያሳጣው ስጋታቸውን የሚያስቀምጡ አልጠፉም፡፡
ኩባንያው ኤአይ እንዲህ ሳይፈትነው በተረጋጋ ኢኮኖሚ ኢንዴክሱ ወደ 500 ከፍ ያለም ነበር፡፡ በ2022 ከ70 በመቶ በላይ እደገት አሳይቷል፡፡በዘርፉ ላይ በርካታ የቴክኖሎጂ ኩባያዎች ሲኖሩ ሲስኮ፣ ዴል፣ ማይክሮሶፍት እና እንዲሁም የAI ቺፕ በማዘጋጀት የሚታወቀው Nvidiaን ጨምሮ ከኤ አይ ጋር የሚመጣጠን ስራ በመስራት ህልውናቸውን ለማስጠበቅ እየታተሩ ናቸው፡፡

በአክሲዮን ገበያውም ኒቪዲያ የተለያዩ ዲዛይኖችን በማዘጋጀት በአምስት ዓመታት ወደ 4,300 ፐርሰንት የሚጠጋውን የአክሲዮኖች ድርሻ ሲይዝ፤የኔትወርክ አገልግሎት የሚሰጠው ሲስኮ (CSCO.O) ደግሞ 4,500 ፐርሰንት መሻገሩን የሮይተርስ ዘገባ ያሳያል፡፡እንደ አማዞን (AMZN.O) ያሉ በርካታ የኢንተርኔት አክሲዮን ላይ የሚሰሩ ኩባንያዎችም ዶት ኮምን መገዳዳር ቢችሉም በጠንካራ ፉክክር ቆይቷል፡፡
አሳሳቢው የAI እድገት ግን ለዶት ኮም በብል እንዲሁም ለሌሎች ቴክኖሎጂዎጂ ኩባያዎች ፈተና መሆኑ አይቀሬ መሆኑን ሮይተርስ አስነብቧል፡፡ አርቴፊሻል ኢንተለጀንሲ ዶት ኮምን ስራ ተቆጣጥሮ ከገበያው እንዳያስወጣው ስጋት ቢቀመጥም ድርጅቱ በ2024 በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂው ዘርፍ 32 በመቶ እድገቱን አሳይታል፡፡ እድገቱ ግን ከሌሎች አመት አንፃር ዝቅተኛ ነው፡፡
ከፈረንጆቹ 2000 ወዲህ እንደ ማይክሮሶፍት ፣አፕል ፣ኒቪዲያ ያሉ ግዙፍ ኩባንያዎች ከ20 በመቶ በላይ እድገት ማሳየታቸው መረጃው ይጠቁማል፡፡በአክሲዮን ገበያው ዶት-ኮም ከሚያገኘው ገቢ ይልቅ Nvidia እና Cisco የተሻለ እድገት ማሳየታቸው ለዶት ኮም ስጋት መሆኑ አይቀሬ ነው፡፡
ግራፊክስ ማቀናበሪያ (ጂፒዩዎችን)፣ የፕሮግራም አፕሊኬሽን እንዲሁም የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ቺፕን በማዘጋጀት እውቅናን ያተረፈው ኒቪዲያ ኩባንያ ከወቅቱ ጋር እኩል መራመድ የቻለ ኩባንያ ተደርጎ የቀረበ ነው፡፡ ኒቪዲያ ጊዜውን ያገናዘበ የኤአይ ቺፕስን በማዘጋጀት የተሻለ ቁመና ላይ ይገኛል፡፡

የኒቪዲያ የገበያ ዋጋ ጭማሪ ያሳየው በኤአይኤ ተፈላጊ የሆኑ የቺፕስ ፍላጎትን በማቅረቡ ነው፡፡ ይህም በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የሚስተዋለውን ውድድርና በአለም ኢኮኖሚ የሚጫወተውን ሚና አጉልቶ ያሳየ ነው ተብሏል፡፡የኒቪዲያ አክሲዮኖች በ 3.5 የጨመረ ሲሆን የገበያ ዋጋውም ወደ 3.34 ትሪሊዮን ዶላር አድጓል፡፡ ይህም ኒቪዲያ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስን መምጣት ለትርፋማነቱ እንደ ጥሩ አጋጣሚ መጠቀሙን አመላካች ነው፡፡
ኔቪዲያ በዎል ስትሪት ከፍተኛ ግብይት የተከናወበት ኩባንያ ሆኗል ፣በየቀኑ በአማካይ 50 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ሲያገኝ አፕል ፣ማይክሮሶፍት እና ቴስላ እያንዳንዳቸው 10 ቢሊዮን ዶላር ገደማ አግኝተዋል ተብሏል፡፡ከአምናው ጋር ሲነጻጸር በዚህ ዓመት የማይክሮሶፍት አክሲዮኖች 19 በመቶ ገደማ ጭማሪ ሲያሳያዩ የኒቪዲያ አክሲዮን በሦስት እጥፍ ገደማ ጭማሪ በማሳየት በዘጠኝ ወራት ከ1 ትሪሊዮን ዶላር ወደ 2 ትሪሊየን ዶላር ከፍ ብሎ ተወዳዳሪነቱን አጠናክሯል እተባለ ነው፡፡ ኔቪዲ በ40 እጥፍ ወደፊት የገቢ እድገት ያሳያል ተብሎ ተቀምጧል፡፡
በአጠቃላይ ኤ አይ ለቴክኖሎጂ ኩባያዎቹ ስጋት ብቻ ሳይሆን ጥሩ እድልም ይዞ እንደመጣ የኒቪዲያ ተሞክሮ ሲያሳይ ፤ በቀደመው አሰራራቸው ላይ የቀጠሉ ኩባንያዎች ግን ቀጣይነታቸውን አጠያያቂ ያርገዋል ሲል ሮይተርስ ለዶት ኮም ማሳሰቢያ አዘል መልዕክት አስተላልፏል፡፡ተቋማቸውን ግዜው ጋር ያላሻሻሉ ኩባያዎች ደግሞ የገቢ ማሽቆልቆል አጋጥሟቸው የሰራተኛ ቅነሳ ለማድግ መገዳዳቸው አይቀሬ ነው ተብሏል፡፡












