፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሰኔ 27 2016| NBC ETHIOPIA- ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማብራሪያቸው ኢትዮጵያ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ካስመዘገበቻቸው ስኬቶች አንዱ የኢንዱስትሪ እምርታ ነው ብለዋል።
የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄን ጨምሮ የዘርፉን ምርታማነት ለማሳደግ በተወሰዱ እርምጃዎች ዘንድሮ በአምራች ዘርፉ ትልቅ ስኬት መመዝገቡን ተናግረዋል።
በዚህም ዘርፉ ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር 10 ነጥብ 1 በመቶ ዕድገት ማስመዝገቡንም ጠቅሰዋል።በዘንድሮው ዓመት 390 ፋብሪካዎች ወደ ስራ መግባታቸውንም አስታውሰዋል።
በትግራይ ክልል 217 ፋብሪካዎች ወደ ስራ መመለሳቸውን ገልጸው፤ በአጠቃላይ የፋብሪካዎች ምርታማነት መጨመር በተኪ ምርቶች እና በወጪ ምርቶች ላይ ትልቅ ውጤት መመዝገቡን ነው ያነሱት።

በነባር ሲሚንቶ ፋብረካዎች 30 በመቶ የምርት ዕድገት መመዝገቡን ጠቅሰው አሁን ያለውን ሀገራዊ የሲሚንቶ ምርት 50 በመቶ የሚሸፍን አዲሱ የለሚ ሲሚንቶ ፋብሪካ በቅርቡ ይመረቃል ብለዋል።
መንግስት በዘርፉ ላይ ያደረጋቸው ድጋፎች ለኢንዱስትሪዎች ምርታማነት ትልቅ ዕገዛ ማድረጋቸውንም ገልጸዋል።በኢንዱስትሪ ፓርኮች ለአምራቾች ከማቅረብ ባሻገር የነጻ ንግድ ቀጣናዎችን በማጠናከር ከፍተኛ የኢንቨስትመንት ፍላጎት እያመጣ ስለመሆኑም ጠቅሰዋል።
ዘንድሮ የተገኘውን ዕድገት በማስቀጠል ቀጣይነት ያለው ፈጣን ኢኮኖሚ ለማረጋገጥ እንደሚቻልም ነው ያነሱት።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












