፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሰኔ 27 2016| NBC ETHIOPIA- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 36ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ከም/ቤቱ አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ እየሰጡ ነው፡፡
???? ለውጡ በፖለቲካው መስክም ከኤርትራ ከኬንያም ከጫካም ያሉትን ጋብዟል፤
???? የሰላም ችግር በአገራችን ውሎ ያደረ ስር የሰደደ በሽታ ነው፤
???? ኢትዮጵያ ውስጥ ከ50 ዓመት በፊት መፈንቅለ መንግስት አንዴ ተሳክቷል፣ አሁን ግን ጭራሽ አይሳካም
???? እኛ ወታደሮች ነን መፈንቅለ መንግስት እንዳይሳካ አድርገን ነው ተቋማትን የሰራነው
???? አንድ እንሁን ሰብሰብ እንበል የጋራ አገር ነው ያለን፤
???? በአማራም በኦሮሚያም ክልል ያለው ችግር በሁለት ተከፍሎ የሚታይ ነው፤
???? አንደኛው ዱር ግባ የሚል ፕሮፖጋንዳ ሰለባ ነው፤ ሁለተኛው ደግሞ ጥራኝ ዱሩ የሚል ነው፤
???? አማራ ኦሮሚያ ትግራይ ሰላም ካልሆነ የመጨረሻ ተጎጂ እኛ ነን፤ ያሰብነውን መስራት አንችልምና፤
???? በፕሪቶሪያ ስምምነት ምክንያት ተኩስ ቆሟል፤ የሚሞት ሰው ቆሟል፤ የታሰሩ ተፈተዋል፤ የቆሰሉ ታክመዋል፤ ከስራ የታገዱ ስራ ይዘዋል፤ የተለያዩ ቤተሰቦች ተገናኝተዋል፤
???? በራያና ጸለምት የተፈናቀሉ ሰዎች እየተመለሱ ነው፤
???? በትግራይ የሽግግር መንግስት በህወሓት ዋና ዋና መሪዎች ላይ እምነት አለኝ፤ ችግሩ በሰላም እንዲፈታ ፍላጎት አላቸው፤
???? አሁንም ግን እልህኘነትና ቁጣ ያላቸው አሉ፤ ይሄ አካሄድ ይጎዳል፤
???? እኛ አማራም በኦሮሚያም በትግራይም ግጭት አንፈልግም፤












