፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሰኔ 25 2016| NBC ETHIOPIA-የምሥራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ኃይል ልዑክ በኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ኃይል ሞተራይዝድ ሻለቃን ጎበኘ።

በኬኒያ ናይሮቢ ከሚገኘው የምሥራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ኃይል ቢሮ የተውጣጣ ልዑክ ኢትዮጵያ ለምሥራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ኃይል የምታዋጣውን ሞተራይዝድ ሻለቃ የግዳጅ ዝግጁነት የሚያረጋግጥ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መግባቱ ይታወቃል።
በምሥራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ኃይል ዳይሬክተር ብርጋዴር ጀኔራል ፖል ካሁሪያ ጀማ የተመራው የተጠባባቂ ኃይሉ ልዑክ በኢትዮጵያ ቆይታው ቢሸፍቱ የሚገኘውን የኢትዮጵያ የምሥራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ኃይል ሞተራይዝድ ሻለቃ ጠቅላይ ጦር ሰፈር ተገኝቶ የሻለቃዋን ዝግጁነትና አጠቃላይ ቁመና መጎብኘቱን ኢዜአ ዘግቧል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












