፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሰኔ 25 2016| NBC ETHIOPIA-6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን በ35ኛ መደበኛ ስብሰባው ዛሬ በልዩ ልዩ አጀንዳዎች ላይ ይወያያል።
ምክር ቤቱ ቀዳሚ ባደረገው አጀንዳው የፌዴራል መንግስት የ2017 በጀት አመት ረቂቅ በጀት ላይ በዝርዝር ይወያያል።
በመቀጠል በኩዌት እና በኢትዮጵያ መካከል በሥራ ስምሪት ዘርፍ የተፈረመውን የመግባቢያ ሰነድ ለማጽደቅ የሚቀርበውን ረቂቅ አዋጅ መርምሮ የሚያፀድቅ ነው የሚሆነው።
በተጨማሪም የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት እንደገና ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅን እንዲሁም የኢሚግሬሽን አዋጅን ለማሻሻል የወጣ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ ረቂቅ አዋጁን ያፀድቃል።
????YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
???? TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
????Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
????Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












