፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሰኔ 19 2016| NBC ETHIOPIA- የዊክሊክሱ መስራች ጁሊያን አሳንጅ ከእስር ተለቆ አውስትራሊያ ገባ፡፡
በሰሜናዊ ማሪያና ደሴቶች በሚገኝ ፍርድ ቤት በአንድ ክስ ተወንጅሎ ለዓመታት የዘለቀው ጉዳዩ ተቋጭቶለታል ተብሏል ፡፡
አሳንጅ የአሜሪካን ምስጢራዊ ሰነዶች አሳልፎ ለዓለም ሰጥቷል በሚል በ18 ክሶች መወንጀሉ ይታወሳል ፡፡
የዊክሊክሱ መስራች ጁሊያን አሳንጅ ሰኞ ከብሪታንያ ከወጣ በኋላ የመጨረሻውን የፍርድ ሂደት በሰሜናዊ ማሪያና ተከታትሎ አውስትራሊያ ገብቷል ፡፡
ጁሊያን አሳንጅ በአውስትራሊያ ደማቅ አቀባበል የተደረገለት ሲሆን የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ለሙያው የከፈለው ዋጋ ነው በሚል ምስጋናቸውን እየቸሩት ነው፡፡
አሜሪካ ከብሪታንያ ተላልፎ ሊሰጠኝ ይገባል በሚል ስትወተውት ብተሰነብትም በመጨረሻ አሳንጅ ካንበኔራ ገብቷል ፡፡
ግራ ዘመም የአውሮፓ ፓርላማ ዓባላት የስፔኑ ፕሬዚዳንት ፔድሮ ሳንቼዝ መርከቧ መልህቋን እንዳትጥል በደብዳቤ ማሳሰባቸውም ይታወሳል ፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












