፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሰኔ 18 2016| NBC ETHIOPIA-35ተኛው የአፍሪካ ኒኩልየር ሳይንስና ቴክኖሎጂ የምርምር ልማት(AFRA) Technical working Group Meeting (TWGM) ጉባኤ በአዲስ አበባ ሀይሌ ግራንድ ሆቴል እየተካሄደ ነው።
ጉባኤውን የኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከAFRA ጋር በመተባበር ነው ያዘጋጀው።



የኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በልጠ ሞላ (ዶ/ር) የአፍሪካ ኒኩልየር ሳይንስና ቴክኖሎጂ የምርምር ልማት ፕሮግራም በአፍሪካ ለሚታዩት የተለያዩ ችግሮች መፍትሄ እንደሚሆን በመጠቆም ፣ ኢትዮጵያም የተለያዩ ፕሮጀክቶችን እየሰራች መሆኑን ተናግረዋል።
ጉባኤው የአፍሪካ ሀገራት የኒኩልር ቴክኖሎጅን ለችግሮቻቸው መፍቻ ለማድረግ የሀሳብ ልውውጥ የሚደረግበት እና ሀገራቱ በዘርፉ እየስሯቸው ያሉት ስራዎችን የሚያቀርቡበት ነው።

በመርሃግብሩ የኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች፣ የአፍሪካ ሀገራት የAFRA ተወካዮችን እንዲሁም ዓለም አቀፍ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
በ-ሰላም ይልማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












