፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሰኔ 14 2016| NBC ETHIOPIA-“ቴክኒና ሙያ ለዘላቂ ልማት” በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው የቴክኒክና ሙያ ሳምንት በአዲስ አበባ የሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ቤቶች ስራዎቻቸውን ለእይታ ያቀርቡበታል።
የአዲስ አበባ የቴክኒክና ሙያ ቢሮ ባዘጋጀው መድረኩ ሀገር በቀል ስራዎች ይቀርቡበታል ተብሏል።
በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ለህብረተሰቡ ማሳወቅና ግንዛቤ ማስጨበጥ የቴክኒክና ሙያ ሳምንት ዓላማ ነው ተብሏል።
ዓመታዊውና ዘንድሮ ለ14ኛ ጊዜ የሚካሄደው ሳምንቱ ከሰኔ 15 እስከ ሰኔ 20 በኤግዚቢሽን ማዕከል የሚካሄድ ይሆናል።
በ-መቅደስ ደምስ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












