፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ግንቦት 21 2016| NBC ETHIOPIA- ግንባታው ከተጀመረ 13 አመታትን ያስቆጠረው ታላቁ የህዳሴ ግድብ አጠቃላይ የግንባታ ደረጃ 96 በመቶ ያህል መጠናቀቁ ተገልጿል።
ቀሪው የግድቡ 4 በመቶ ግንባታ በአንድ አመት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ የተገለፀ ሲሆን ለዚህም 40 ቢሊየን ብር እንደሚያስፈልግ ነው የተገለፀው።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ግድቡን ለማጠናቀቅ የሚያስፈልገውን ገንዘብ ለማሰባሰብ የሚያስችል itsmydam.com የተሰኘ መተግበሪያን ይፋ አድርጓል።
መተግበሪያውን ስራ የማስጀመሪያ መርሃ ግብርም እየተከናወነ ሲሆን አስተዋፅኦ ላበረከቱ የዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት እውቅና የመስጠት መርሃ ግብር በመካሄድ ላይ ይገኛል።
በ-አክረም ኑርያ
????YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
???? TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
????Website – https://nbcethiopia.com/news/
????Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












