፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ግንቦት 03 2016| NBC ETHIOPIA- የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ፍልስጤምን 194ኛ የድርጅቱ አባል ለማድረግ የቀረበለትን የድጋፍ ውሳኔ ሀሳብ በከፍተኛ ድምጽ ማሰለፉ ተገለጸ።
ጠቅላላ ጉባኤው የአባልነት ጥያቄውን ለሚወስነው የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት የፍልስጤምን የአባልነት ጥያቄ መልሶ እንዲያጤነው ሀሳብ አቅርቧል ነው የተባለው ።
በአረብ ሀገራት እና በፍልስጤም የተደገፈው የውሳኔ ሀሳብ በ143 የድጋፍ ድምጽ፣ በ9 ተቃውሞ እና በ25 ድምጸ ተአቅቦ መጽደቁ ታውቋል ።
አሜሪካን ጨምሮ እስራኤል፣ አርጀንቲና፣ ቼቺያ፣ ሀንጋሪ ፣ እንዲሁም ፓፑዋ ኒው ጊኒ እና ሌሎች ሀገራት የውሳኔ ሀሳቡን ተቃውመውታል ተብሏል ። ፍልስጤም በፈረንጆቹ ከ2012 ጀምሮ የታዛቢነት ስፍራ ተሰጥቷት እንደነበር ይታወቃል፡ ፡
አሜሪካ ከዚህ በፊት ጥያቄውን ውድቅ አድርጋው የነበረ ቢሆንም አርብ ዕለት በነበረው የድምጽ መስጠት ጉባኤ ላይ ግን ይህንን መብቷን አልተጠቀመችም ሲል ያስነበበው ቢቢሲ ነው ፡፡ ቶማይ መኮንን
????YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
???? TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
????Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
????Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












