አዲስ አበባ | ግንቦት 01 2016| NBC ETHIOPIA-ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የአለማችን ቢሊየነሮች በሀገራቸው ኢኮኖሚያዊ እድገት ላይ ያላቸው ሚና በእጅጉ ከፍ እያለ ይገኛል፡፡ በዓለማችን በሕዝብ ብዛት ቀዳሚ በሆነችው ህንድ የሚገኙ ቱጃሮችም የሀገሪቱን ኢኮኖሚ በበላይነት በመቆጣጠር ላይ መሆናቸው መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስቴር ናሬንድ ሞዲ ፤ የህንዱ ቁጥር አንዱ ቢሊየነር ሙከሽ አምባኒ እና የአዳኒ ቡድን መስራች ጋውታም አዳኒ ሀገሪቱ የአለም ኢኮኖሚን በበላይነት እንደትመራ ለማስቻል እየሰሩ ነው ሲል ሲ ኤን ኤን በቢዝነስ አምዱ አስነብባል፡፡
የ67 አመቱ የህንድ ቁጥር አንድ ቢሊየነር አምባኒ ከወራት በፊት ማርክ ዙከርበርግ፣ ቢል ጌትስ ጨምሮ በርካታ ታዋቂ ሰዎች በተገኙበትና አለምን ጉድ ያስባለ ስርግ መደገሳቸው ይታወሳል፡፡ ለሶስት ቀን በቆየው የቅድመ ሰርግ ስነ-ስርዓት የአምባኒን አለም አቀፋዊ ታዋቂነትን እና ተፅዕኖ ፈጣሪነቱን በይበልጥ አጉልቶ ያሳየነ ነበር፡፡ አምባኒን በህንድ በተለያዩ የንግድና ኢንቨስትመንት ስራዎች ላይ ተሰማርቶ የሚገኝ ሲሆን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ እድገት ሚና እየተጫወተ መሆኑ ይገለፃል፡፡

እንዲሁም የአዳኒ ቡድን መስራች የሆኑት ቢሊየነር ጋውታም አዳኒም በህንድ ኢኮኖሚ ለማሳደግ አሻራቸውን እያኖሩ መሆኑን ባለሙያዎች ይገልፃሉ፡፡ባለሀብቱ በ2024 77.6 ቢሊዮን ዶላር ሀብት ያስመዘገበ ሲሆን ባለፉት አስርት ዓመታት ውስጥ ባሳየው ከፍተኛ እድገት ዓለምን አስደምሟል። እ.ኤ.አ በ2022 የአለማችን ሁለተኛ ሀብታም የነበረውን ጄፍ ቤዞስን በመብለጥ ለአጭር ጊዜ የሁለተኛ ስፍራነትን ተቆጣጥረው ነበር፡፡
ህንድን ለሶስተኛ ጊዜ ለመምራት በተከታታይ ዘመቻ በማካሄድ ላይ የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ለህንድ ሁለማናዊ እድገት ቅድሚያ ለሚሰጣጥሙ ድርጅቶችና ኢንቨስትመንቶችን ሲያበረታቱ ቆይተዋል። ህንድ በደቡብ እስያ ከሚገኙ ሀገራት መካከል በ21ኛው መቶ ዘመን በኢኮኖሚ ጠንካራ ለማድረግ ታቅዶ እየተሰራ ነው፡፡ ይህም በቻይና ኢንቨስትመንት ለማግኘት በአቅርቦት ሰንሰለት ውስጥ ያለውን ተግዳሮት ለመቀነስ ለሚፈልጉ አምራቾች ትክክለኛ አማራጭ ለመስጠት ተዘጋጅቷል ነው የተባለው፡፡
የሬሊየንስ ኢንዱስትሪዎችና የአዳኒ ቡድን እያንዳንዳቸው ከ200 ቢልዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ፈሰስ በማድረግ ከንጹሕ የኃይል ምንጮች አንስቶ እስከ መገናኛ ብዙኃንና ቴክኖሎጂ ድረስ ባሉ መስኮች ተሰማርተው ይገኛሉ፡፡ ይህም በሀገሪቱ ኢኮኖሚ እንቅስቀሴ ላይ ያላቸው ተፅእኖ ከፍ እንዲል ማስቻሉ ነው የሚነገለፀው፡፡
በዚህ ምክንያት ሞዲ ፣ አምባኒ እና አዳኒ በመጪዎቹ አስርት ዓመታት ውስጥ የህንድ ኢኮኖሚያዊ ኃያልነት ለመቅረጽ መሰረታዊ ሚና እየተጫወቱ ነው ይላል የሲ ኤን ኤን ዘገባ፡፡
በህንድ የኢኮኖሚ ዋና ከተማ በሆነችው ሙምባይ የሁለቱ ነጋዴዎች አሻራ በአዳኒ ከተያዘው አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ጀምሮ በሁሉም ቦታ ይገኛል። ህንድ በአለም ፈጣን ኢኮኖሚ እያደጉ ካሉ ሀገራት አንዷ ነች ፤ በ2023 3.7 ትሪሊዮን ዶላር አመታዊ እድገትን ያስመዘገበች ሲሆን በሞዲ አሥር ዓመታት ውስጥ አራት ደረጃዎችን በማሻሻል ዩናይትድ ኪንግደምን በመብለጥ በዓለም አምስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡
የህንድ የነፍስ ወከፍ የሀገር ውስጥ ምርት እ.ኤ.አ. በ 2014 እና 2023 መካከል በ 55% አድጓል ። እንዲሁም ከሌሎች ዋና ዋና ኢኮኖሚዎች ጋር ሲነፃፀር በጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ከፍተኛ እድገት አሳይታለች።













