፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሚያዚያ 16 2016| NBC ETHIOPIA- የአሜሪካ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት በሀገሪቱ ቲክቶክን ሊያግድ የሚችል አዋጅ አጽደቀ።
አዋጁ የቲክቶክ ባለቤት የሆነውን ባይትዳንስ የማህበራዊ ትስስር ገጹን ድርሻ በ9 ወራት ውስጥ የማይሸጥ ከሆነ ቲክቶክ በአሜሪካ አገልግሎት እንዳይሰጥ እንደሚያግድ ተገልጿል።
አዋጁ ወደ ፕሬዝዳንት ባይደን የተመራ ሲሆን፤ እንደደረሳቸው ፊርማቸውን በማስቀመጥ ሕግ እንደሚያደርጉት መናገራቸው ታውቋል።
አሜሪካ ቲክቶክ እንዲሸጥ ባይትዳንስ ላይ ጫና ማድረግ ቢሳከላት እንኳን ለሽያጩ ሂደት የቤጂንግ ባለስልጣናት ይሁንታ ያስፈልጋል ተብሏል ። ሆኖም ቻይና ይህንን ዓይነቱን ውሳኔ እንደምትቃወም ገልጻለች።
አዋጁን ከሕግ መወሰኛ ምክር ቤቱ 79 የምክር ቤት አባላት ሲደግፉት 18 የሚሆኑት ደግሞ ተቃውመውታል ሲል ቢቢሲ አሰነብቧል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












