፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሚያዚያ 04፣ 2016| NBC ETHIOPIA-‘በመረጃ ላይ የተመረኮዘ ውሳኔ ለተሻለ የጤና ስርዓት’ በሚል መሪ ሀሳብ 2ኛ ሀገር አቀፍ የጤና መረጃ ስርዓት የውይይት መድረክ በመካሄድ ላይ ነው።
በኢትዮጵያ ያለው የጤና መረጃ ስርአት ለማዘመን ብሎም ዲጂታላይዝድ ለማድረግ እንቅስቃሴ እየተደረገ እንደሚገኝ በጤና ሚኒስቴር የዲጂታል ጤና መሪ ስራ አስፈጻሚ ገመቺስ መልካሙ ተናግረዋል ። የጤና መረጃ ስርዓትን ዲጂታላይዝድ በማድረግ 4 ሺህ የጤና ተቋማትን በኔትወርክ ማስተሳሰር መቻሉ ተገልጿል ።

የጤና መረጃ ስርዓትን ለማሻሻል በተጀመረው “ዲኤችአይኤስ ቱ” መተግበሪያ አማካኝነት ባለፉት ስምንት ዓመታት አንድ ቢሊየን ያህል መረጃ መሰብሰብ መቻሉ በመድረኩ ተገልጿል።
በ-ሰላማዊት ወልደገሪማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












