አዲስ አበባ | የካቲት 08፣ 2016| NBC ETHIOPIA -አገልግሎቱ ነገና ከነገ በስቲያ ለሚካሄደው ለ37ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ መሪዎች አዲስ አበባ እየገቡ መሆኑን አስታውቋል።
በ37ተኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ 49 የአፍሪካ አገራት እንደሚሳተፉ የተገለፀ ሲሆን ከሌሎች የአለም አገራት 6 መሪዎች እና 13 የአለም አቀፍ ድርጅት መሪዎች እንደሚሳተፋ ይጠበቃል ሲሉ የአገልግሎቱ ሚኒስቴር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ ተናግረዋል።
ሚኒስቴር ዴኤታዋ ከጉባኤው ጎን ለጎን የዲጂታላይዜሽን መስፋፋት ለአፍሪካ ትራንስፎርሜሽን እና የአፍሪካን የምግብ ሉአላዊነት ማረጋገጥ የሚሉ ሁለት ጉባኤዎች በኢትዮጵያ አማካኝነት እንደሚዘጋጁም በመግለጫቸው ጠቁመዋል።
በ-ሔርሜላ ፍቃደ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












