አዲስ አበባ | የካቲት 07፣ 2016| NBC ETHIOPIA -የሶማሊያ ባለስልጣናት በሞቃዲሾ ለደህንነት ሲባል የፊት ጭምብል የሚያደርጉ ዜጎች እንዳይጠቀሙ መከልከላቸው ተገለጸ ፡፡
የመቃዲሾ ቃል አቀባይ ሳላህ ዲሪ ጭምብል በማድረግና ማንነትን በመሸፈን በሞቃዲሾ ከፍተኛ ወንጀል እየተፈጸመ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
እ.ኤ.አ በ2019 ከኮሮና ወረርሽኝ ጋር ተያይዞ ጭምብል ማድረግ የተጀመረ መሆኑን በመግለጽ አሁን ግን ወንጀለኞች ራሳቸውን በጭምብል እየደበቁ ጥቃት እደረሱ ስለሆነ፤ መንግስት ለመከልከል እንደተገደደ ቃል አቀባዩ ገልጸዋል፡፡
የሶማሊያ መንግስት እንዳስታወቀው ከጭምብል ባሻገር የራስ ቆብና ጦር መሳሪያ ይዞ በህዝብ ትራንስፖርት አካባቢ መገኘት ተከልክሏል፡፡ ዘገባው የቢቢሲ ነው ፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












