አዲስ አበባ | የካቲት 05፣ 2016| NBC ETHIOPIA -ቢላሉል ሀበሺ የልማትና መረዳጃ እድር ከሀይፕሮፋይል ጋር በመተባበር ከየካቲት 22 እስከ መጋቢት 1/2016 የረመዳን ወር ባዛር ሊያካሂድ መሆኑን አስታውቋል::
በባዛሩ ላይ ከ300 የሚልቁ የሀገር ውስጥና የውጭ አምራች ኢንደስትሪዎች, አስመጪና ላኪዎች፤ አከፋፋዮች እንዲሁም አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶችን ጨምሮ በርካታ ተቋማት ይሳተፉበታል ተብሏል::
የረመዳን ወር ከመግባቱ አስቀድሞ የሚካሄደው ባዛር ለረመዳን የሚያስፈልጉ እቃዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለተገልጋዮች የሚቀርብበት መሆኑ ተመላክቷል::
ከባዛሩ የሚገኘው ገቢም በዋናነት ቢላሉል ሀበሺ የልማትና መረዳጃ እድር ለሚያከናውናቸው የበጎ አድራጎት ስራዎች የሚውል እንደሆነ ተጠቁሟል::
ከተመሰረተ 25 አመታትን በማስቆጠር ላይ የሚገኘው ቢላሉል ሀበሺ የልማትና መረዳጃ እድር በችግር ውስጥ ለሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች በንፁህ መጠጥ ውሃ, በትምህርት, በተጨማሪም በገንዘብ ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱ ተገልጿል::
በ- አክረም ኑርያ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












