አዲስ አበባ | ጥር 29፤ 2016| NBC ETHIOPIA- የሩሲያና ዩክሬን ጦርነት ዛሬም እንደቀጠለ ነው፡፡ እልባት አልባው ጦርነት ብዙ ሰባዊና ማህበራዊ ምስቅልቅል አስከትሏል፤ በዓለማችን ኢኮኖሚ ላይም የራሱን ጥቁር ጥላ እያሳረፈ ይገኛል፡፡

የሩሲያው ቪላድሜር ፑቲን ባለፈው ወር ዩክሬንን እንደሚበቀሉ መዛታቸውን ተከትሎ ሩሲያ ዩክሬንን አብዝታ እያጠቃች ትገኛለች ።
የሩሲያ ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን በሩሲያዋ ቤልጎሮድ ከተማ 24 ሰዎችን ገድሏል ላሉት የዩክሬን ጥቃት የአጸፋ ምላሽ መስጠት ከጀመሩ በኋላ በኪቭ እና ካርኪቭ ከተሞች ላይ ሩሲያ ከፍተኛ ድብደባ እያደረሰች መሆኑን የዩክሬን ባለስልጣናት መናገራቸው ይታወሳል፡፡
ዩክሬን ከካርኪብ ግዛት ጥቃት እንደሰነዘረችባት የምትገልጸው ሩሲያ በግዛቷ ላይ መጠነ
ሰፊ ጥቃት አድርሳለች።
ተባብሶ በቀጠለው ጦርነት የሩሲያ ማጥቃት አሁንም አልቆመም፤የኬቭ ከንቲባ ቪታሊ ክሊሸንኮ በምስራቅ ማይካሎቭ ግዛት፤ የሩሲያ ሚሳኤል፤ በመኖሪያ ቤቶችና በኤሌክትሪክ ሀይል መተላለፊያ መስመሮች ላይ ጉዳት ሲያደርስ በአንድ ሰው ላይ ሞት አስከትሏል ሲሉ ተናግረዋል ፡፡
በጥቃቱ ከሰው ህይወት ህልፈት ባሻገር ዘጠኝ ሰዎች ቁስለኛ መሆናቸው ታውቋል፡፡ ብዙ መሰረተ ልማቶች መውደማቸውም ተሰምቷል ፡፡
እንደ ዩክሬን ባለስልጣናት ከሆነ የሩሲያ ክሩዝ ሚሳኤል በምዕራብ ግንባር በሊቪቭ፤ ተርኖፕሊ እና በኢቫኖ ፍራንክቭስክ ተከታታይ ጥቃት እየፈጸመ ነው ለዚህ ምላሽ የሚሆን መከላለከል እያደረጉ ይገኛሉ፡፡
ሩሲያ ከ158 በላይ ሚሳዔልና ድሮኖች ኪቭን ጨምሮ በተለያዩ የዩክሬን ከተሞች ለይ መጠነ ሰፊ ጥቃት ማድረጓ በተለያዩ መገናኛ ብዙሀን ተዘግቧል፡፡ ነገር ግን የዩክሬን አየር ኃይል ሩሲያ ከተኮሰቻቸው 158 ሚሳዔሎች ና ድሮኖች መካከል ውስጥ 114 የሚሆኑት ተመትተው ወድቀዋል ሲል አስታውቆ ነበር ። ሆኖም ሩሲያ ሀይሏን አጠናክራ ጥቃት እየፈጸመች ነው ፡፡
ሩሲያ የሚሳዔል እና የድሮን ጥቃቶቹን የዩክሬን ዋና ከተማ ኪቨን ጨምሮ በኦዴሳ፣ ደናይፕሮፕትሮስቮክ፣ ክሃርኪቭ እና ለቪቭ ከተሞች ላይ አድርሳለች ።
የዩክሬን ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ሩሲያ ያላትን ሁሉንም ዓይነት የጦር መሳሪያዎችን እተጠቀመች ነው ያሉ ሲሆን፤ በጥቃቱም መኖሪያ ቤቶች አና የእናቶች ሆስፒታሎች መመታታቸውን አስታውቀዋል።
ሩሲያ ሃይፐረሶኑክ፣ ክሩዝ እና ባላስቲክ ሚሳዔሎችን ተጠቅማለች ያሉ ሲሆን፤ በተለይም በአየር ላይ ለማክሸፍ ከባድ የሆነውን X-22 ሚሳዔል ተጠቅማለች ብለዋል ።
ሩሲያ በፈረንጆቹ የካቲት 2022 ዩክሬንን ማጥቃት ከጀመረችበት አንስቶ በተደጋጋሚ የሚሳኤልና የድሮን ጥቃቶችን እያደረገች ትገኛለች፡፡
ሩሲያ ልዩ ተልዕኮ በሚል ነበር ዩክሬን ላይ ዘመቻ የጀመረችው። በአጭር ጊዜ ይጠናቀቃል የተባለው ጦርነት ግን አሁን ላይ ቀጥሎ እየተካሄደ ነው።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












