አዲስ አበባ | ጥር 17፤ 2016| NBC ETHIOPIA- አሜሪካዊው የህግ ታራሚ በናይትሮጂን ጋዝ በሞት እንዲቀጣ የተፈረደበት የመጀመሪያው ሰው መሆኑ ተገለጸ።

ኬነት ዩጂን ስሚዝ የተባለው ግለሰብ በ1989 በቅጥር ነፍሰ ገዳይነት ተሰማርቶ የአንድ ሰባኪ ሚስት በመግደል ነበር ክስ ተመስሮተበት ማረሚያቤት የገባው ።
በግድያ ወንጀል ጥፋተኛ የተባለው ስሚዝ በአሜሪካ በናይትሮጂን ጋዝ የሞት ቅጣት የተፈጸመበት የመጀመሪያው ሰው ሲሆን የሞት ቅጣቱ የተፈጸመውም በአልባማ ግዛት ነው ተብሏል፡፡
በፈረንጆቹ 2022 የአልባማ ግዛት ግለሰቡን በመርፌ በሞት ለመቅጣት ያደረገው ሙከራ ደም ስሩን ማግኘት ባለመቻሉ ድርጊቱ ሳይፈጸም ቀርቶ እንደነበር ታውቋል።
የ58 ዓመቱ የኬነት ስሚዝ ግድያ ሲፈጸም አምስት ጋዜጠኞች መገኘታቸውንም ቢቢሲ በዘገባው አመላክቷል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook- https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












