አዲስ አበባ | ጥር 17፤ 2016| NBC ETHIOPIA-በቅርብ ጊዜ የተደረጉ ጥናቶች እንሚያሳዩት የስማርት ስልክ ተጠቃሚዎች በቀን በአማካይ 4 ስአት ከ30 ደቂቃዎችን ስልካቸው ላይ ያጠፋሉ።ይህ በአማካይ ስልክ ሚወራበትን ጊዜ እንደማይጨምር መረጃው ያመለክታል።

የስማርት ስልክ አጠቃቀማችን የሚከታተሉ፣ በቁጥር የተደገፉ መረጃዎች እየሰጡ የስማርት ስልክ አጠቃቀማችን እንድናስተካክል ሰአታችን በአግባቡ እንድንጠቀም የሚያግዙን መተግበሪያዎችን ዘርዝረናቸዋል።
1.Forest

ይህ መተግበሪያ የስማርት ስልክ አጠቃቀማችን ጨዋታ በመሰለ ቁምነገር ነው እንድናስተካክል የሚያግዘን። አረንጓዴ ገጽታ ያለው ፎረስት መተግበሪያ ስልካችን መጠቀም ስንጀምር የዛፍ ዘር ሲዘራ ያሳያል፤ ከጥቂት ቆይታ በኋላም ፍሬው ማደግ ይጀምራል፤ የዛፍ መልክ እየያዘም ይሄዳል።
በዚህ መተግበሪያ አጠቃቀማችን እንዲገደብ ያደረግናቸው (እንደ ፌስቡክና ቲክቶክ ያሉ መተግበሪያዎችን) ከልክ በላይ መጠቀም ስንጀምር ግን ዛፉ እየጠወለገ ሄዶ ይወድቃል።
2. SPACE

የስማርት ስልካችን አጠቃቀም በመቆጣጠር ጊዜያችን የሚበሉትን የሚጠቁመን “ስፔስ” ሁነኛ መተግበሪያ ነው።
ይህ መተግበሪያ ፌስቡክ ወይንም ቲክቶክ በቀን ውስጥ በምንፈልገው መጠን ገደብ አስቀምጠን እንድንጠቀም ያስችላል፤ ቀኑን ሙሉ ልንጠቀማቸው የማንፈልጋቸውንም መርጠን መዝጋት የሚያስችል አማራጭ አለው።
3. one sec

4. AppBlock

በስልካችን ውስጥ ያሉ እያንዳንዱን መተግበሪያ አጠቃቀም መረጃ በመሰብሰብ እያዘናጋን ያለውን መተግበሪያ ቢዘጋ መልካም ነው የሚል ምክረሃሳብ ያቀርባል። በዚህም ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ማገድ አልያም የምንጠቀምበትን የጊዜ ገደብ ማስቀመጥ ያስችላል።
አፕብሎክ” ስያሜውም እንደሚያመላክተው ከልክ በላይ እየተጠቀምናቸው ያሉ መተግበሪያዎችን ለመዝጋት የሚውል ነው።
5. OffScreen

ይህ መተግበሪያ የስልካችን ስክሪን ለምን ያህል ጊዜ እንደበራና ምን አይነት መተግበሪያዎች እንደተከፈቱ እየተከታተለ ዓይናችን ብሎም ጠቅላላ ጤናችን የሚታደጉ እርምጃዎችን እንድንወስድ ያግዘናል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook- https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












