-አዲስ አበባ | ጥር 08፤ 2016| NBC ETHIOPIA – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከዓለም ኢኮኖሚ ፎረም ፕሬዚዳንት ቦርግ ብሬንድ ጋር ውይይት ተወያዩ፡፡
-ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በስዊዘርላንድ ዳቮስ እየተካሄደ ባለው የዓለም ኢኮኖሚ ፎረም ላይ እየተሳተፉ ነው።
-በጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሠ የተመራ የከፍተኛ አመራሮች ልዑክ በአዋሽ አርባ የሚገኘውን የሜካናይዝድ ኃይልን ጎበኘ፡፡
-በቅርቡ ከሶማሊላንድ ጋር የተፈረመው ሁሉን አቀፍ የትብብርና አጋርነት ሰነድ በጋራ መልማትን የሚያረጋግጥ መሆኑን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዲማ ኖጎ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
-በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ስድስት ወራት ለ779 ሺህ በላይ ተማሪዎች የምገባ አገልግሎት መሰጠቱን የከተማ አስተዳደሩ ምገባ ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡
-የድንቅነሽ (ሉሲ) ቅሪተ-አካል የተገኘበት 50ኛ ዓመት ዝክረ-በዓል እየተካሄደ ነው። ቅሪተ-አካሉን ባገኙት ፕሮፌሰር ዶናልድ ጆሃንሰን የተመራው ልዑክ በብሔራዊ ሙዚየም ጉብኝት እያደረገ ይገኛል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












