አዲስ አበባ | ታህሳስ 26፤ 2016| NBC ETHIOPIA -የሱዳን መንግስት በኬንያ የሚገኙትን የሀገሪቱን አምበሳደር ለምክክር መጥራቱን ገለጸ፡፡

የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ በኬንያ ናይሮቢ የሚገኙትን አምባሳደሩን ወደ ካርቱም እንዲመለሱ የተጠሩት ለምክክር እና የኬንያ መንግስት ለሱዳን ፈጠኖ ደራሽ ሃይሎች አዛዥ ሌተናል ጀነራል መሀመድ ሃምዳን ዳጋሎ ላደረገችው ይፋዊ አቀባበል ተቃውሞ ለመግለጽ ነው።
የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው፤ የኬንያ መንግስት በሌተናል ጀነራል መሀመድ ሃምዳን ዳጋሎ በሚመራው የፈጥኖ ደራሽ ኃይል የተፈጸሙ ዘግናኝ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን እንዲሁም በሀገሪቱ እና በዜጎች ላይ የደረሰውን ጉዳት ዘንግቷል ብሏል።
ሱዳን ከናይሮቢ አምባሳደሯ ጋር የሚኖራት ምክክር በሱዳን እና በኬንያ ግንኙነት የወደፊት እጣ ፈንታን የሚወስን እንደሆነም የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመግለጫው አስታውቋል።
ጄነራል ሃምዳን ዳጋሎ ዘጠኝ ወራት ካስቆጠረው ጦርነት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በኡጋንዳ፣ ኢትዮጵያ እና ጂቡቲ እንዲሁም ባሳለፍነው ረቡዕ በኬንያ ጉብኝት አድርገዋል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












