ድሬደዋ | ጥቅምት 29 2016| NBC ETHIOPIA – የክቡር ዶክተር አርቲስት አሊ ቢራ የህይወት ታሪክ እና ይሰራቸው የነበሩ ስራዎችን ብሎም የሱን ራዕይ ለማስቀጠል ያለመ የፖናል ውይይት በድሬደዋ ከተማ ተካሄደ።

በውይይቱ የኢትዮጵያ ሙዚቃን በማሳደግ ረገድ አርቲስት አሊ ቢራ ያበረከተው አስተዋጽኦ ዘመን የማይሽረው ስለመሆኑ ተመላክቷል።
ውይይቱን በንግግር የከፈቱት የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ ከድር ጀዋር የአርቲስት አሊ ቢራ ሳምንቱን ሲዘከር አዲሱ ተተኪ ትውልድ የእሱን ተምሳሌት በመላበስ ፍቅር መቻቻልን እንዲላመዱ ያስፈልጋል ብለዋል።
አርቲስቱ ከጥበብ ስራዎች በተጨማሪም በተለያዩ በጎ ስራዎች ውስጥ ግንባር ቀደም ተሳታፊ መሆኑን አንስተው የአሊ ቢራን ሌጋሲዎች ለማስቀጠል አስተዳደሩ በትኩረት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።


በፓናሉ ላይ ጥናታዊ ጽሁፍ ያቀረቡት የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት የባህልና ሚዲያ ጉዳዬች አማካሪ የክቡር ዶክተር መሀመድ አህመድ አሊ ቢራ የኢትዮጵያ ሙዚቃ እንዲያድግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል በተለይም በተለምዶ አምስት የነበሩትን የኢትዮጵያ የሙዚቃ ኖቶችን ወደ ሰባት በማሳደግ አለማቀፍ ተሰሚነት እንዲኖረው አድርጓል ብለዋል
አሊ ቢራ በስድስት የተለያዩ ቋንቋዎችን በመዝፈን ህብረ ብሄራዊነትን ሲያቀነቅን የነበረ ስለመሆኑ እና ለመላው የሰው ልጅ እኩልነት ሲታገል ብሎም ስለ ሰው ልጅ ፍቅር ወንድማማችነት በሙዚቃዎቹ ሲሰብክ የቆየ ስለመሆኑ በውይይቱ ወቅት ተገልጾል።
በሄርሜላ ፍቃደ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












