አዲስ አበባ | ጥቅምት 28፤ 2016| NBC ETHIOPIA – “ምክክር – ለወል እዉነቶች” በሚል በሀገራችን በተለያዩ ጊዜያት የሚደረጉ ሀገራዊ ምክክሮች የተሳኩ እንዲሆኑ መደረግ ስላሉባቸዉ ሁኔታዎች በአዲስ አበባ ባህል ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ የተዘጋጀ የዉይይት መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

ዉይይቱ የኢትዮጵያን ቀጣይነት ለማረጋገጥ ፋይዳዉ የጎላ እንደሆነ የተጠቀሰ ሲሆን ለዉይይቱ ግብዐት የሚሆኑ መነሻ ሀሳቦች በተለያዩ ግለሰቦች ቀርቧል።
ሀገራዊ ምክክሩ መፍትሄ እንዲኖረዉ ሊደረጉ የሚገቡ ተግባራት በርካታ መሆናቸዉ በመነሻ ሀሳቡ ላይ ቀርቧል። ከነዚህም ዉስጥ ችግሮቻችን ቀድመን የፈጠርናቸዉ በመሆኑ ምንጫቸው ላይ መስራትና የተሳሳቱ እይታዎችን ማረም ዋነኛ ጉዳዮች መሆናቸዉ ተጠቅሷል።
የወል እዉነታዎቻችንን መለየትና በዛም ላይ የሰረፀ እይታ እንዲኖር ማድረግ ላይ ትኩረት ሊሰጠዉ እንደሚገባም ተነስቷል።
የወል እዉነታዎቻችን ሊፈትኑ የሚችሉ በርካታ ዕንቅፋቶች ሲከሰቱብን የምንፈታበት ቁልፉ መሣሪያ ምክክርና መግባባት ሊሆን እንደሚገባ በመድረኩ አፅንኦት ተሰጥቶታል።
በሊያ ክብሮም
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram –https://t.me/nbcethiopiatv












