አዲስ አበባ | ጥቅምት 27፤ 2016| NBC ETHIOPIA – የአፍሪካ ከተሞች ለንፁህ አየር በሚል የC40 cities ፕሮግራም በአዲስ አበባ ወርክሾፕ እያካሄደ ነው።

ፕሮግራሙ በከተሞች ለጤና ተስማሚ የሆነ አየር ጥራት እንዲኖር ለማድረግ ያለመ ነው ከተሞች ተገቢውን የአየር ጥራት መሳሪያ በመትከል ልኬት በማድረግ መረጃን መሰብሰብ ፣መከታተል ና ማሻሻል እንዲችሉ ያደርጋል ተብሏል።
በመርሃግብሩም ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ከተሞች የተወጣጡ ተሳታፊዎች የተገኙበት ወርክሾፕ በአዲስአበባ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጠና እና C40 cities በጋራ በመሆን ተዘጋጅቷል።

መርሃግብሩም ለ3 ቀናት የሚቆይ ሲሆን የተለያዩ የከተሞች የልምድ ልውውጥ የሚደረግበት ፣ አዲስአበባ እንደ ከተማ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ እየሰራች ያለውን ስራ ለማስቃኘት እንዲሁም በዘርፉ ላይ የሚታዩ ችግሮችን ለመቅረፍ ይረዳል ተብሏል።
በሰላም ይልማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Telegram -https://t.me/nbcethiopiatv
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc/












