አዲስ አበባ | ጥቅምት 27፤ 2016| NBC ETHIOPIA – ከ169 የመንግስት መስሪያ ቤቶች መካከል 164ቱ ወደ ሲስተም ሲገቡ የተቀሩት አምስት ተቋማት ብቻ ወደ ሲስተሙ አለመግባታቸውን የመንግስት የኤሌክትሮኒክ ግዥና ንብረት ባለስልጣን አስታወቀ::
ወደ ኤሌክትሮኒክ የግዥ ስርዓት ያልገቡት አምስት የመንግስት መስሪያ ቤቶች በትግራይና በአማራ ክልል የሚገኙ ሲሆን ወደ ሲስተሙ ያልገቡትም ከወቅታዊ የሰላም ጉዳይ ጋር በተያያዘ እንደሆነ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሐጂ ኢብሳ ተናግረዋል::
የኤሌክትሮኒክ የግዥ ስርዓት ብልሹ አሰራርን ለመቆጣጠርም ሆነ የወረቀት አሰራርን ለመቀነስ ያለው አስተዋፅኦ ከፍ ያለ መሆኑንም ዳይሬክተሩ አብራርተዋል::
የመንግስት የኤሌክትሮኒክ ግዥና ንብረት ባለስልጣን ከተለያዩ የንግዱ ማህበረሰብ ተወካዮች ጋር የኤሌክትሮኒክ ግዥ ስርዓትን አስመልክቶ ምክክር በማካሄድ ላይ ይገኛል::
በአክረም ኑርያ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram –https://t.me/nbcethiopiatv












