አዲስ አበባ | ጥቅምት 19 2016| NBC ETHIOPIA – የመጀመሪያዉ ሃገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ንቃተ ህሊና ላይ የተደረገዉ ጥናት ይፋ በተደረገበት መድረክ ንግግር ያደረጉት የኢፌዴሪ መንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ ዓለም በቴክኖለጂ እያደረገችበት በሚገኘዉ በዚህ ወቅት እኛን መሰል በቴክኖሎጂዉ ያበለፀጉ አገሮች በሳይበር ጥቃት ፈተና ነዉ ብለዋል፡፡ በሀገር ደረጃ ለሳይበር ምህዳሩ ትልቅ ትኩረት በማድረግ መሰራትም ይጠይቃል ሲሉ አፅንኦት ተጥተዋል፡፡

መንግስት የሳይበር ምህዳሩን ለማስተካከል እና ከሳይበር ጥቃት ለመታደግ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እና አርቴፊሻል ኢንተለጀንሲን የማጠናከር ስራዎች እያከናወነ ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ሰለሞን ሶካ በበኩላቸዉ የቴክኖለጂ ተደራሽነት እያደረጉ በመምጣጡ የሳይበር ጥቃት በዛዉ ልክ እየጨመረ በመሆኑን ተናግረዋል፡፡
በተያዘዉ 2016 ሩብ ዓመት ብቻ 2556 የሳይበር የጥቃት ሙከራዎች መደረጋቸዉንን አንስተዋል፡፡

4ተኛዉ ሃገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር 3ተኛ ሳምንት ላይ ይገኛል፡፡ አይበገሬ የሳይበር አቅም ለአገር ሉዓላዊነት በሚል መሪ ቃል ነዉ ሳይበር የደህንነት ወር እየተከበረ የሚገኘዉ፡፡
በሰላም ይልማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












