አዲስ አበባ | ጥቅምት 14፤ 2016|- በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከበረው የዓለም የፖሊዮ ቀን ‹‹በጋራ ፖሊዮን ጨርሰን እናጥፋ›› በሚል መሪ ሀሳብ በኢትዮጵያ እየተከበረ ይገኛል። እለቱንም በማስመልክት በሀገራችን የፖሊዮ በሽታ የህብረተሰቡ የጤና ችግር እንዳይሆንና ጨርሶ እንዲጠፋ ለማድረግ ያለመ ምክክር የጤና ሚኒስቴር ከባለድርሻ አካላት ጋር እያከናወነ ይገኛል።


በሀገራችን ከ1 ሚሊዮን በላይ ህፃናት ምንም አይነት የፖሊዮ ክትባት ማግኘት እንዳልቻሉ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ በውይይቱ አንስተዋል። የፖሊዮ በሽታ አሁንም ድረስ ባላደጉት ሀገራት ኢትዮጵያን ጨምሮ በአሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተመላክቷል።
የክትባት አገልግሎት በጥራት አለመሰጠት እና በጦርነት አካባቢዎች የክትባቱ አለመዳረስ ለበሽታው መስፋፋት ጉልህ ሚና እንዳላቸው ተገልጿል።
በኢትዮጵያ ከፖሊዮ በተጨማሪ የጋንግሪን በሽታ በአሳሳቢ ደረጃ እንደሚገኝ እና ጨርሶ ለማጥፋት ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑን በምምክር መድረኩ ተነስቷል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook- https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram – https://t.me/nbcethiopiatv












